1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግሪክና የዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት ዉዝግብ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 1 2007

በግሪክና በዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት ዉዝግብ ላይ ለመምከር ትናንት ብራስልስ ላይ ባስቸኳይ የተጠራዉ የመሪዎች ስብሰባ ግሪክ እስከነገ ሐሙስ ድረስ ከአበዳሪዎቿ ጋ ሊያስማማት የሚችል የድርድር ሃሳብ እንድታቀርብ በማስጠንቀቅ ተጠናቋል።

https://p.dw.com/p/1FvCH
Alexis Tsipras EU-Parlament
ምስል Reuters/V. Kessler

ባለፈዉ እሁድ በግሪክ የተካሄደዉ የአበዳሪ ድርጅቶችን ቅድመ ሁኔታ የመቀበል ያለመቀበል ሕዝበ ዉሳኔ ከስልሳ ከመቶ በላይ የሚሆነዉ የግሪክ ሕዝብ ቅድመ ሁኔታዉን መቃወሙ ከታወቀ በኋላ በግሪክ፤ በአበዳሪዎቿና በዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት መካከል ያለዉ ግንኙነት አጣብቂኝ ዉስጥ በመግባቱ ነበር ስብሰባዉ የተጠራዉ። በአሁኑ ወቅት ግሪክ ዉስጥ ባንኮች ተዘግተዋል። የኤኮኖሚ እንቅስቃሴዉም ቆሟል። ይህ ችግሯ ባፋጣኝ ካልተፈታም ግሪክ ከዩሮ ልትወጣ ልትገደድ፤ ሕዝቡም ለከፋ ችግር ሊጋለጥ ይችላል የሚል ስጋት አለ።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ