1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግሪክ አበዳሪዎች የደረሱበት ስምምነት

ሰኞ፣ ሐምሌ 6 2007

የአውሮፓ ህብረት የዮሮ ቡድን ሀገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች እና መሪዎች በግሪክ ቀውስ ላይ ለረዥም ሰዓታት ከተደራደሩ በኋላ ዛሬ ማለዳ ለግሪክ የ3ኛ ዙር ብድር ለመስጠት ከስምምነት ደርሰዋል።

https://p.dw.com/p/1Fy1J
Belgien Euro-Gipfel erzielt Einigung bei Griechenland Pressekonferenz
ምስል picture-alliance/dpa/O. Hoslet

[No title]

የትናንት ሌሊቱ ጉባኤ ለግሪክ የብድር ጥያቄ የመጨረሻ ውሳኔ ከመስጠት ባሻገር፤ ግሪክ በዩሮ ዞን ትቆይ ወይስ ለተወሰኑ ዓመታት ለቃ ትውጣ የሚሉ ጥያቄዎችም ያስተናገደ ነበር። ግሪክ ከአበዳሪዎቿ የተጣሉባትን ቅድመ ሁኔታዎች በመቃወሟ የብድር እና ርዳታ መርሃ ግብሮች ተቋርጠው ፤ የግሪክ ባንኮች ተዘግተው መሰንበታቸው ይታወሳል። ግሪክ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ከ82 እስከ 86 ቢሊዮን ዮሮ ብድር እንድታገኝ አበዳሪዎቿ ቢፈቅዱም፤ የግሪክ ፓርላማ አበዳሪዎቿ አያይዘው ያቀረቡትን ቅድመ ሁኔታ እስከ እሮብ ድረስ ማፅደቅ ይኖርበታል። የግሪክ ተጨማሪ የብድር ጥያቄን አስመልክቶ ባለፉት ሁለት ቀናት ብራስልስ የተካሄደውን የዩሮ ሸርፍ አባል ሃገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች እና የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ፤ በስፍራው የሚገኘው ገበያው ንጉሴ ተከታትሏል።


ገበያው ንጉሴ

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ