1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግሪክ የገንዘብ ቀውስ የኢጣልያ ችግርና የዩሮ እጣ ፈንታ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 28 2004

ከዛሬ 10 ዓመት አንስቶ የዩሮ ተጠቃሚ የሆነችውን የግሪክ የገንዘብ ቀውስ ለመፍታት የአውሮፓ ህብረት ከጣለባት ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ ሃገሪቱ ወደ 78 ቢሊዮን ዩሮ እንድትቆጥብ ያስቀመጠው ግዴታ ይገኝበታል ።

https://p.dw.com/p/RvS5
ምስል picture alliance/ZB

በዚህ የቁጠባ እርምጃ ውስጥ የሰራተኛና የደሞዝ እንዲሁም የጡረታ አበል ቅነሳ ይካተታል ። እነዚህና የመሳሰሉት የአውሮፓ ህብረት ለግሪክ ያስቀመጣቸው ቅድመ ግዴታዎች የግሪክን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ምን ያህል ይረዳሉ ። በቀጣይነት የገንዘብ ቀውስ ሊገጥማት ይችላል የምትባለው የኢጣልያስ ይዞታ ምን ይመስላል የዩሮ የወደፊት እጣስ ምን ይሆናል ? በጀርመን የተለያዩ ዩኒቭርስቲዎች የሚያስተምሩትን የበርሊኑን የምጣኔ ሃብት ምሁር ዶክተር ፈቃዱ በቀለ ን ጋብዥያለሁ ዶክተር ፈቃዱ በቅድሚያ ህብረቱ ለግሪክ ያስቀመጣቸው ቅድመ ግዴታዎችና ሊያስከትሉ የሚችሉት ችግሮች ያስረዳሉ ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ