1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግራሲያኒ መታሰቢያና ተቃዉሞዉ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 24 2004

የፌዛን-ሊቢያና የኢትዮጵያ አራጅ በሚል ለሚወገዘዉ ለቀድሞዉ የኢጣሊያ የጦር ማርሻል ለሩዶልፎ ግራሲያኒ መታሰቢያ ሐዉልት መቆሙና ቤተ-መዘክር መከፈቱን አንድ ብሪታንያዊ የታሪክ ሙሑርና የኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር ተቃወሙት።

https://p.dw.com/p/160VG
Yekatit 12 Denkmal“ in Addis Abeba, Äthiopien. Denkmal für Gefallene, die gegen Faschismus gekämpft haben Thema: „Yekatit 12 Denkmal“ in Addis Abeba. Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn_DW Schlagwörter: Addis Abeba „Yekatit 12 Denkmal
ምስል DW

የፌዛን-ሊቢያና የኢትዮጵያ አራጅ በሚል ለሚወገዘዉ ለቀድሞዉ የኢጣሊያ የጦር ማርሻል ለሩዶልፎ ግራሲያኒ መታሰቢያ ሐዉልት መቆሙና ቤተ-መዘክር መከፈቱን አንድ ብሪታንያዊ የታሪክ ሙሑርና የኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር ተቃወሙት።በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት ኢትዮጵያዉያን አርበኞችን በመርዝ ጢስ ያስፈጀዉና የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በጅምላ ላስጨፈጨፈዉ ለግራሲያኒ በቅርቡ በትዉልድ መንደሩ አፊሌ ዉስጥ መታሰቢያ ተቋማት ተከፍተዉለታል።ብሪታንያዊዉ የታሪክ ሙሑርና የኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር ፕሬዝዳት በየፊናዉ እንዳሉት ለጦር ወንጀለኛዉ መታሰቢያ መዘጋጀቱ ሰዉዬዉ ያደረሰዉን ግፍ መዘንጋት ነዉ።ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።በተያያዘ ዘገባ ልግራሲያኒ የቆመለት የመታሰብያ ሃዉልት እና በስሙ የተከፈተዉ ፓርክ በአለም ዙርያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንን አስቆጥቶአል። ይህንኑ ድርጊት በመቃወም በተለያዩ አገሮች የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል። የአለም ሰላም ወዳድ ህዝብን ድጋፍም እያሰባሰቡ ነዉ። በተለይ ለንደን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለነገ ሰላማዊ ሠልፍ ለማድርግ መዘጋጀታቸዉን አስታዉቀዋል።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ