1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግራዚያኒ መታሰቢያና ተቃዉሞዉ

ረቡዕ፣ የካቲት 13 2005

በሃያ-አምስት ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ተቃዉሟቸዉን በያሉበት አሰምተዋል።በየከተሞቹ የተሰበሰቡት ወይም አደባባይ የወጡት ኢትዮጵዉያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የኢጣሊያ መንግሥትና የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ለፋሽስቱ የጦር መሪ መታሰቢያ መቆሙን እንዲቃወሙ አቤት ብለዋልም።

https://p.dw.com/p/17iMP
ምስል picture-alliance / dpa


ለፋሽስት ኢጣሊያ የጦር መሪ ለማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ መታሰቢያ ቤተ-መዘክርና መናፈሻ መሰየሙት በመቃወም ዉጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የሚያደርጉት ሠልፍና ጥያቄ እንደቀጠለ ነዉ። በግራዚያኒ የታዘዘዉ የፋሽት ኢጣሊያ ጦር በብዙ ሺሕ የሚቆጠር የአዲስ አበባና የአካባቢዋን ሕዝብ የጨፈጨፈበት ዕለት ትናንት ሲታሰብ፥ በሃያ-አምስት ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ተቃዉሟቸዉን በያሉበት አሰምተዋል።በየከተሞቹ የተሰበሰቡት ወይም አደባባይ የወጡት ኢትዮጵዉያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የኢጣሊያ መንግሥትና የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ለፋሽስቱ የጦር መሪ መታሰቢያ መቆሙን እንዲቃወሙ አቤት ብለዋል።ዋሽግተን ዲሲ የተደረገዉን ሠልፍ አበበ ፈለቀ ተከታትሎት ነበር። ሥለ ሠልፉ ሒደትና ዉጤት በስልክ ጠይቄዋለሁ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ