1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብርና መረጃ በነፃ የሚቀርብበት ነፃ የስልክ መስመር

ሐሙስ፣ መስከረም 22 2007

ይህ በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የተጀመረው 8028 አዲስ ነጻ የስልክ መስመር ነው። ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እገዛና ምክር የሚያገኙበት ነጻ የስልክ መስመር ግልጋሎት ከተጀመረ ጥቂት ወራት ተቆጠሩ።

https://p.dw.com/p/1DPAm
Symbolbild Festnetz Telefon
ምስል Gajus - Fotolia.com

በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የመንግስትና ህዝባዊ ተቋማት ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት አቶ አበበ አወቀ እንዳስታወቁት፣ በኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር፤የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩትና ኢትዮ ቴሌኮም ትብብር የተጀመረውና የግብርና ትራንፎርሜሽን ኤጀንሲ የበላይነት የሚመራው የ8028 ነጻ የስልክ መስመር ግልጋሎት ለአርሶ አደሮች ብቻ የታሰበ አይደለም። የግብርና ባለሙያዎችም ሆኑ በዘርፉ መረጃ የሚፈልጉ ዜጎች ባሉበት ሆነው በመደወል የሚፈልጉትን ማግኘት እንደሚችሉ ነው አቶ አበበ ያስታወቁት።

Äthiopien, Alltag, Bauer, Bäuerin
ምስል Peter Zimmermann

8028 ነጻ የስልክ መስመር ከቅድመ-ምርት እስከ ድህረ ምርት ባለው ሂደት አስፈላጊ መረጃዎችን ለአርሶ አደሮች ያቀርባል። አሁን በአማርኛ፤ኦሮሙኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎች ግልጋሎት የሚሰጠው 8028 በአርሶ አደሮች ዘንድ ከፍተኛ ተባይነት ማግኘቱን አቶ አበበ አወቀ ገልጸዋል።

አርሶ አደሮች በተዘጋጁት 90 የስልክ መስመሮች ቀድመው በተቀረጹ ድምጾች አስፈላጊ መረጃዎችን ያገኛሉ። በተለያዩ የግብርና ጊዜያት ለገበሬው አስፈላጊ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ወቅታዊ የጽሁፍ መልዕክቶችም ይላካሉ። እስካሁን ወደ 8028 ከደወሉት መካከል 87 በመቶው ገበሬዎች ናቸው። እስካሁን በሶስት ቋንቋዎች የሚቀርበው ግልጋሎት እንደ አስፈላጊነቱ ሊያድግ እንደሚችል አቶ አበበ አወቀ አስረድተዋል።

እሸቴ በቀለ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ