1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትርና የ«ህዳሴው ግድብ»

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 18 2010

በህዳሴው ግድብ ላይ ውይይት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ የተገኙት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ሳሜኅ ሹክሪ አዲስ ያሉትን ሐሳብ መሰንዘራቸው ተዘግቧዋል።

https://p.dw.com/p/2q0GZ
Äthiopien Grand Renaissance Staudamm al-Sisi al-Bashir Desalegn
ምስል Ashraf Shazly/AFP/Getty Images

የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው አዲስ ያሉትን ሐሳብ አቀረቡ

ውጭ ጉዳይ ሚንሥትሩ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የሚያደርጉት ውይይት ለዉጤት እንዲበቃ  «ገለልተኛ» ያሉት የዓለም ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል። የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትርን ሐሳብ በተመለከተ  የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንሥቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለምን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬያቸው ነበር።  «የሦስትዮች  ብሔራዊ ኮሚቴ ሥራውን አኹንም እንደቀጠለ ነው» ያሉት አቶ መለስ  «ይኽ ባለበት ኹኔታ ሌላ የሚታሰብ ነገር የለም» ሲሉ  አክለዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ