1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብጻውያን ተቃውሞ እና የጦር ኃይሉ ሚና

እሑድ፣ ጥር 29 2003

በፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባራክ ላይ የተነሣውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የሀገሪቱ ገዢ ፓርቲ አመራር ስልጣኑን ለቋል። የተቃዋሚ የሙስሊም ወንድማማችነት ቡድንም ምክትል ፕሬዚደንት ኦማር ሱሌይማን ያቀረቡትን ጥሪ በመቀበል ከሀገሪቱ መንግስት ጋ ውይይት ጀምሮዋል።

https://p.dw.com/p/QyMZ
ምስል picture alliance / dpa

ፕሬዚደንት ሙባራክ ግን አሁንም ስልጣናቸውን አልለቀቁም። በመሆኑም የህዝቡ ተቃውሞ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ያም ቢሆን ግን የግብጽ ጦር ኃይል የሀገሪቱ ፕዚደንት ስልጣናቸውን እንዲለቁ በመጠየቅ አደባባይ በመውጣት ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ባለው በሀገሪቱ ህዝብ አንጻር እስካሁን አንዳችም የኃይል ርምጃ አልወሰደም። በፕሬዚደንት ሙባራክ አንጻርም አልቆመም። የጦር ኃይሉ በአሁኑ የህዝብ ዓመጽ ወቅት የሚጫወተው ሚና የብዙዎችን ትኩረት ስቦዋል።

አርያም ተክሌ
መስፍን መኮንን