1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፅና የእስራኤል ግንኙነት

ማክሰኞ፣ መስከረም 2 2004

የእስራኤል ጦር ከወር በፊት አምስት የግብፅ ጠረፍ ጠባቂ ወታደሮችን በስሕተት መግደሉ ያስቆጣቸዉ ግብፃዉያን ካይሮ የሚገኘዉን የእስራኤል ኤምባሲን ባለፈዉ ሳምንት ከወረሩ ወዲሕ ከካይሮ የወጡት የእስራኤል ዲፕሎማቶች እስካሁን ወደ ግብፅ አልተመለሱም።

https://p.dw.com/p/RlRr
ምስል dapd


በእስራኤል ኤምባሲና ዲፕሎማቶች ላይ የተቃጣዉ ጥቃት ሌላ መዘዝ እንዳያስከትል ለመከላከል የሁለቱ ሐገራት መንግሥታት እየጣሩ ነዉ።ሁለቱም ከዚሕ በፊት ለተፈራራሙት የሠላም ዉል ገቢራዊነት በፅኑዕ መቆማቸዉን አስታዉቀዋል።የሐይፋ-እስራኤሉ ወኪላችን ግርማዉ አሻግሬ እንደሚለዉ የጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔትንያሁ መንግሥት ጉዳዩን ወደ ማለዘቡ አዘንብሏል።ግርማዉን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ግርማ አሻግሪ
ነጋሽ መሃመድ