የግብፅና የዩናይትድ ስቴትስ መሪዎች ዉይይት
ረቡዕ፣ ነሐሴ 13 2001ማስታወቂያ
ካለፈዉ ቅዳሜ ጀምሮ ዩናይትድ ስቴትስን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የግብፅ ፕሬዝዳት ሆስኒ ሙባረክ ትናንት ከጋባዣቸዉ ከፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ጋር ተነጋግረዋል።የሁለቱ መሪዎች ዉይይት የኢራንን የኑክሌር መርሐ-ግብርና የሱዳንን ሁኔታ መነካካቱ ባይቀርም-ዋናዉ ትኩረት የፍልስጤም እስራኤሎች ሠላም ነዉ።ሁለቱን ወገኖች ለመሸምገል የሚደረገዉን ጥረት ኦባማ «አበረታች» ሲሉት፥ ሙባረክ ግን «በመሠረታዊ» ጉዳዮች ላይ ዉይይት መጀመር አለበት ይላሉ።አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
አበበ ፈለቀ /ነጋሽ መሀመድ
አርያም ተክሌ