1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፅ ቀውስና የአውሮፓ ሕብረት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 16 2005

በግብጹ ግጭት መንስኤ አስቸኳይ ጉባኤ ያካሄዱት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባሳለፉት ውሳኔ መሰረት ሕብረቱ ለግብፅ ጦር የሚውሉ የጦር መሣሪያዎችና ወታደራዊ ቁሳቁሶች ሽያጭ አግዷል ። «በሀገር ውስጥ ህዝብን ለመጨቆን የሚውል የማንኛቸውም የጦር መሣሪያዎች የውጭ ንግድ ፈቃዶች» ታግደዋል ።

https://p.dw.com/p/19Ulz
ምስል picture-alliance/AP Photo

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትንናት ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባዔ በግብፅ ላይ የጦር መሣሪያ ሽያጭ እገዳ ለመጣል መስማማታቸውን አስታውቀዋል ። በግብፅ ተጨማሪ ደም መፍሰሱ እንዲያበቃ ሁሉም ወገኖች እንዲደራደሩም ሚኒስትሮቹ ጠይቀዋል ። የአውሮፓ ህብረት ለግብፅ የሚሰጠውን እርዳታ እንደገና እንደሚመረምሩም ተናግረዋል ።
ባለፈው ሳምንት ወደ 900 የሚደርሱ ሰዎችን ህይወት ባጠፋው በግብጹ ግጭት መንስኤ አስቸኳይ ጉባኤ ያካሄዱት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባሳለፉት ውሳኔ መሰረት ሕብረቱ ለግብፅ ጦር የሚውሉ የጦር መሣሪያዎችና ወታደራዊ ቁሳቁሶች ሽያጭ አግዷል ። «በሀገር ውስጥ ህዝብን ለመጨቆን የሚውል የማንኛቸውም የጦር መሣሪያዎች የውጭ ንግድ ፈቃዶች» እንደሚታገድ ህብረቱ በፅሁፍ ያወጣው መግለጫ ያትታል።

Ashton reist zu Krisengesprächen nach Kairo
አሽተን በካይሮምስል Reuters/Amr Abdallah Dalsh

በቅርቡ በወጣ አንድ ዘገባ መሠረት እ.ጎ.አ በ 2011 የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት 303 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 406 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሣሪያና ወታደራዊ ቁሳቁስችን ለግብፅ ሸጥለዋል ። ከህብረቱ አባል ሃገራት ፈረንሳይና ስፓኝ በዋነኛነት እስከ 102 ሚሊዮን ዩሮ የሚያወጡ የጦር አውሮፕላኖችን ለግብፅ የሚሸጡ ሃገራት ናቸው ።የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባልና የፓርላማው የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀ መንበር ኤልማር ብሮክ ህብረቱ ለሃገሪቱ የሚሰጣቸው እርዳታዎች ለአንድ ወገን ጥቅም ብቻ መሆን የለበትም ይላሉ ።
« የአውሮፓ ህብረት ለግብፅ የሚያቀርበው የሙስሊም ወንድማማቾች ማህበርንም ሆነ የግብፅ ጦር ኃይልን ብቻ የሚጠቅም ሊሆን አይገባም »
ሚኒስትሮቹ ከጦር መሣሪያዎች ሽያጭ እገዳ ሌላ የግብፅ ጦር ኃይልና የሙስሊም ወንድማማቾች ማህበር እንዲደራደሩም ጥሪ አቅርበዋል ።

EU-Ukraine Gipfel in Brüssel
ኤልማር ብሮክምስል DW

በአሁኑ ጊዜ ግን የጦር ኃይሉም ሆነ የሙስሊም ወንድማማቾች ማህበር ለውይይት ዝግጁ አይመስሉም ። በዚህ የተነሳም ብሮክ እንደሚሉት የአውሮፓ ህብረት የግብጹን ቀውሱ የመሸምገል እድሉ ውስን ነው ።
« በሁለቱ ወገን ያለው ተቃርኖ እጅግ የከረረ ከመሆኑ የተነሳ አረረም መረረ ትርጉም ያለው ምልክት ለማሳየት ካልሆነ በስተቀር ይህ ነው የሚባል ትርጉም ያለው ተግባር ማከናወን አንችልም »

ብሮክ እንደተናገሩት ሚኒስትሮቹ ትናንት ያሳለፉት የጦር መሳሪያ ሽያጭ እገዳ የተባባሰውን የግብጽ ብጥብጥ ለማርገብ ይረዳል፣ አንድ አይነት ተፅእኖም ሊያሳድር ይችላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል ። ሁለቱ ወገኖች መጨካከናቸውን ወደ ጎን ትተው እንዲነጋገሩም ያበረታታቸዋል የሚል እምነትም አለ ። የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ ካትሪን አሽተን ከህብረቱ የደቡባዊ ሜዴቴራንያን ሃገራት ተወካይ ቤርናርዶ ሊዮን ጋር ባለፈው ሐምሌ 2 ጊዜ ግብፅ ሄደው ሁለቱ ወገኖች ፖለቲካዊው ውይይት እንዲካሂዱ ለማደፋፈር ሞክረው ነበር ። ይሁንና ሰላማዊ መፍትሄ ሊገኝ አልቻለም ።ከብራሰልሱ ጉባኤ በፊት ጀርመንን የመሳሰሉ ሃገራት ለግብፅ የሚሰጠው የልማት እርዳት እንዲቀነስ ሃሳብ አቅርበው ነበር ። ይህ ግን የሁሉንም ድጋፍ አላገኘም ። ከሃሳቡ ተቃዋሚዎች ውስጥ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አባል ማይክል ጋህለር ይገኙበታል።« የአውሮፓ ህብረት ህዝቡን በቀጥታ የሚረዱትን ለምሳሌ በትምሕርትና በጤና ዘርፍ ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶችን መቀጠል አለበት ። ይህ ለግብጽ ህዝብ ግልፅ ምልክት ይሆናል ።»
የሚጋጩት ወገኖች የሚነጋገሩበት ፣ ሃገሪቱም ወደ ዲሞክራሲያዊ ጎዳና የምትመለስበትን መንገድ መፈለጉ አሁን ለግብፅ ወሳኝ ነው ። ይህ ተግባራዊ እንዲሆን መጣር ይገባናል ይላሉ ጋህለር ።
«ሃገሪቱ ወደ ቀድሞው መረጋጋት መመለስ እንድትችል ሁሉም ወገኖች ብሔራዊ ውይይት እንዲያካሂዱ ማደፋፈር የኛ ድርሻ ሊሆን ይገባል ። »
የግብፅ ፖለቲካዊ ሁኔታ ባለበት ከቀጠለ በሃገሪቱ ኤኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ይሆናል ። ሃገሪቱ አለመረጋጋቷ የውጭ ባለሃብቶችን ያርቃል ። ስለዚህ በጋህለር እምነት የአውሮፓ ህብረት ገለልተኛ አቋም ይዞ ህዝቡን መደገፍና ዲሞክራሲያዊ መንግሥት እንዲቋቋም መርዳት ይጠበቅበታል ።

Europäische Union Michael Gahler
ማይክል ጋህላርምስል Fethi Belaid/AFP/Getty Images

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ