1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፅ አመፅ በሳምንቱ መጀመሪያ

ማክሰኞ፣ የካቲት 1 2003

ግብፅ ውስጥ የተቃውሞው ወገን ፤ ተጨማሪ ዐቢይ የፖለቲካ ስብሰባ ከማድረጉ ጥቂት ሰዓቶች ቀደም ብሎ፤አዲሱ ም/ፕሬዚዳንት ዖማር ሱሌይማን በቴሌቭዥን በሰጡት መግለጫ ፣ መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የሥልጣን ሽግግር የሚያደርግበት የጊዜ ሰሌዳ አለው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/Qyqy
የታህሪር አደባባይ ሰኞ ጠዋትምስል dapd

ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ፣ ህገመንግሥቱን የሚያሻሽል ኮሚቴ እንዲሠማራ አዘዋል። በሚሻሻለው ህገ መንግሥት የፕሬዚዳንቱ የአገልግሎት ዘመን ይገደባል። ይሁንና የሲሌልማንን መግለጫ ችላ በማለት ከ 2 ሳምንት በላይ አደባባይ በመውጣት ያቀረብነው ጥያቄ ገና ምልሽ አላገኘም ያሉት የተቃውሞ ሰልፈኞች፤ በካይሮና በሌሎችም ከተሞች አደባባይ መውጣታቸውን እንደገፉበት ናቸው።

ኤስተር ሳውብ

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ