1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፅ አዉሮፕላን ጠለፊ ድራማ አበቃ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 20 2008

የግብፅ የመንገደኞች አዉሮፕላንን ጠልፎ ቆጵሮስ ባሳረፈዉ ግለሠብ እና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል የነበረዉ ፍጥጫ እና ድራማ አበቃ።

https://p.dw.com/p/1ILYa
Flugzeug von EgyptAir am Flughafen Kairo
ምስል Getty Images/AFP/Kh. Desouki

የቆፕሮስ እና የግብፅ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት አዉሮፕላን ጠላፊዉ ለፀጥታ አስከባሪዎች እጁን በሠላም ሰጥቷል።ከአሌክሳንደሪያ ወደ ካይሮ ይበር የነበረዉን አዉሮፕላን ከነመንገደኞቹ ጠልፎ ቆፕሮስ ያሳረፈዉ ግለሠብ አብዛኞቹን መንገደኞች ለቅቆ አራት የአዉሮፕላኑን ባልደረቦችና ሰወስት መንገደኞችን አግቶ ነዉ የዋለዉ። የግብፅ መንግሥት እስረኞችን በተለይ ሴት እስረኞችን በሙሉ ካልለቀቀ ሰባቱን ሰዎችና ራሱን ከነአዉሮፕላኑ በታጠቀዉ ቦምብ ለማጋየት ዉሎዉን ሲዝት ነበር።ጠላፊዉ እጁን ሰጥቶ ድራማዉ ካለቀ በኋላ የቆጵሮስ ፀጥታ አስከባሪዎች እንዳስታወቁት ግለሰቡ የታጠቀዉ ፈንጂ የሌለዉ ዝናር ነበር።ጠላፊዉ እጁን የሰጠበት ምክንያት ግን በግልፅ እልተነገረም።የቆጵሮስ ፕሬዝደንት ኒኮስ አናስታሲዶስ እንዳሉት ደግሞ ግለሰቡ ከሸባሪ ቡድናት ጋር ግንኙነት የለዉም።

ነጋሽ መሀመድ

አርያም ተክሌ