1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግብፅ የፕረስ ነፃነት

ዓርብ፣ ግንቦት 17 2010

የካይሮ ገዢዎች በተለይ የሙስሊም ወንድማማቾች ማሕበረን ሲበዛ ይፈሩታል።እርግጥ ነዉ የማሕበሩን አባላት እና ደጋፊዎች ገድለዉ፤ የተረፉትን አስረዉ፤ ሌሎቹን አሰድደዋል።የማሕበሩን ሐብት ንብረት ወርሰዉ አፈራርሰዉታል።በሕግ አግደዉታልም።ግን ገድለዉትም ይፈሩታል።

https://p.dw.com/p/2yL0y
Ägypten Journalisten protestieren gegen Festnahme zweier Kollegen in Kairo
ምስል Reuters/Staff

Ägypten: Journalist Verurteilt,Blogger verhaftet - MP3-Stereo

የግብፅ መንግሥት በተቺ ጋዜጠኞች እና የአምደ መረብ ፀሐፍት ላይ የሚወስደዉ ጥንካራ እርምጃ እንደቀጠለ ነዉ።መንግሥት ከዚሕ ቀደም የሐገሪቱን ሕግ እና ደንብ ለማፍረስ ከሚያሴር ቡድን ጋር ተባብረሐል ብሎ የከሰሰዉን አንድ ጋዜጠኛ የሐገሪቱ ፍርድ ቤት 10 ዓመት እስራት ፈርዶበታል።የመንግሥትን መርሕ እና ሥራ በመተች የሚታወቅ አንድ የዓምደ መረብ ፀሐፊ ደግሞ ታስሯል።የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንደሚሉት የፕሬዝደንት አብዱል ፈታሕ አልሲሲ መንግሥት የተቃዋሚ እና ተቺ ጋዜቸኞችን ድምፅ ለማፈን የሚወስደዉ እርምጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነዉ።ክርስቲያን ክኒፕ የዘገበዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።

ሁለቱም የሆነዉ ሮብ ነዉ።ጋዜጠኛ ኢስማኢል አሌክሳንድራኒ አስር ዓመት ተፈረደበት።የዓምደ መረብ ፀሐፊ ወኢል አባስ ታሰረ።ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች (RSF-በፈረንሳይኛ ምፃሩ) እንደሚለዉ የግብፅ መንግሥት ያሰራቸዉ ጋዜጠኞች ቁጥር ከኢስማኤል ጋር 27 ሲደርስ፤ የዋሊድ መታሰር ደግሞ እስረኛ የአምደ መረብ ፀሐፊዎችን ቁጥር ስድስት አድርሶታል።

ጋዜጠኛ ኢስማኤል ፍትሕ ሲዛባ፤ፖለቲከኞች ሲቀጥፉ፤ሹመኞች ሲያጭበረብሩ ካየ እና ከሰማ ዝም አይልም።ያጋልጣል።ይተቻልም።ጄኔራል አብዱል ፈታሕ አልሲሲ ከስልጣን ባስወገዷቸዉ በፕሬዝደንት መሐመድ ሙርሲ ላይ የተያዘዉን የወነጀል ጭብጥ ሐሰትነት አጋልጧል።የፍርድ ሒደቱን ኢፍትሐዊነት፤ የተከሳሹ መብት መጣስን ተችቷል።
ሌላዉ ቀርቶ የግብፅ መንግሥት  አሸባሪዎችን መዋጋት በሚል ሰበብ በሐገሪቱ ዜጎች በተለይ በሲና ነዋሪዎች ላይ ይፈፅማል የሚባለዉን ግፍና በደል ደጋግሞ አጋልጧል።ግን ተቃዋሚም፤ ፖለቲከኛም አይደለም።ከአል ሲሲ መንግሥት ጥርስ ለመግባት ግን ተቺ ጋዘጠኛነቱ በቂ ነዉ።ታሰረ።

Mahmoud Abu Zeid Ägypten Kairo Journalisten
ምስል Reuters/A.A.Dalsh

ስሙ ባልተጠቀሰ ቡድን አባልነት፤ ወይም በአባሪ ተባባሪነት፤  የሐገሪቱን ሕግ በመጣስ እና የሐሰት መረጃ በማሰራጨት ሰወስት ወንጀል ተከሰሰ። ሮብ ተፈረደበት።አስር አመት-እስራት።የድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የፕረስ ነፃነት ጉዳይ ኃላፊ ክርስቶፍ ድረየር እንደሚሉት የግብፅ መንግሥት ከሐቅ በራቀ ክስ ጋዜጠኞች የሚያስር እና የሚወነጅለዉ በሥጋት ሥለተወጠረ ነዉ።«ግብፅ ዉስጥ የምናየዉ እወድቃለሁ ብሎ የሚፈራ ሥርዓት ለሕልዉናዉ ሲፍጨርጨር ነዉ።ከሐገሪቱ ፖለቲካዊ ቀዉስ በተጨማሪ የምጣኔ ሐብቱ ድቀት በጣም እየከፋ ነዉ።የሥርዓቱ መሪዎች ተቺዎችን ማለፍ ይፈራሉ።ሙባረክ እንዴት እንደተወገዱ ያዉቁታል።ይሕ እንዲደገም አይፈልጉም።»
የካይሮ ገዢዎች በተለይ የሙስሊም ወንድማማቾች ማሕበረን ሲበዛ ይፈሩታል።እርግጥ ነዉ የማሕበሩን አባላት እና ደጋፊዎች ገድለዉ፤ የተረፉትን አስረዉ፤ ሌሎቹን አሰድደዋል።የማሕበሩን ሐብት ንብረት ወርሰዉ አፈራርሰዉታል።በሕግ አግደዉታልም።ግን ገድለዉትም ይፈሩታል።
ጋዜጠኛ ኢስማኤልንም ሲከሱ-የሙስሊም ወድማማቾችን ሥም ጠቅሰዉ የማሕበሩ አባል ነሕ እንዳይሉት ማሕበሩን  አግደዉታል፤ እንዳይተዉት መወንጀያ ሰበብ አጡ።ስሙን ሳይጠቅሱ የአንድ  ቡድን አባል» አሉት-ለወንጀሉ።

የኢንተርኔት አምደኛ ወኢል አባስ ተቃዋሚ ፖለቲከኛም ነዉ።እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ2011 ፕሬዝደንት ሁስኒ ሙባረክን ከስልጣን ያስወገደዉን ሕዝባዊ አመፅ ሒደት እና ዋና ዋና ክንዋኔዎች ሲመዘግብ ነበር።አሁንም አላቋረጠም።ሮብ ቀን ፖሊሶች ሊይዙት ሲመጡበት እንኳ« ሊያስሩኝ ነዉ» የምትል መልዕክት በፌስ ቡክ ገፁ አስፍሮ ነበር።
የግብፅ ነፃ ጋዜጠኞች እንደሚያሾፉት ወኢል አንድ ወንጀል «በልኩ» ይሰራለታል።የጋዘጠኞች መብት ተሟጋቹ ድርጅት አባል ክርስቶፎ ድረየር እንደሚለሉት ጋዜጠኞችን የአሸባሪ ቡድን ተባባሪ ወይም አባል ብሎ መወንጀል ለግብፅ መንግስት እንግዳ አይደለም።
                                  
«ከዚሕ ቀደም በነበሩ ተመሳሳይ እርምጃዎች፤ የአሸባሪ ቡድን ተባባሪ፤ በጣም ሲከፋ ደግሞ አባል ብሎ በደፈናዉ መወንጀል የተለመደ ነዉ።እነዚሕ ዉንጀላዎች ምንም መሠረት የላቸዉም።አንዳዴ ደግሞ በክሱ ሒደት ይነሳሉ።የመጨረሻ ዓላማዉ (መንግሥት) የማይፈልገዉ መረጃ እንዳይሰራጭ ማፈን ነዉ።»
ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች በቅርቡ ባሰራጨዉ የፕረስ ነፃነት ዝርዝር ግብፅ ከ180 ሐገራት 161ኛ ናት።የፕሬዝደንት አልሲሲ መንግሥት በጋዜጠኞች እና በመገናኛ ዘዴዎች ላይ የሚወስደዉን እርምጃ የተለያ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እያወገዙት ነዉ።

Ägypten: Blogger und Journalist Wael Abbas wurde verhaftet
ምስል picture-alliance/R. Anis

ኬርሽተን ክኒፕ

ነጋሽ መሐመድ 

ሸዋዬ ለገሰ