1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፅ ፕሬዚደንት በጦር ኃይሉ ላይ የወሰዱት ውሳኔ

ሰኞ፣ ነሐሴ 7 2004

የግብፅ ፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ በሀገሪቱ የከፍተኛውን የጦር ኃይሉን ምክር ቤት ሊቀ መንበር እና የመከላከያ ሚንስትር ፊልድ ማርሻል ታንታዊን እና ኤታ ማጆር ሹም ሳሚ አናንን በትናንቱ ዕለት ከጦር ኃይሉ ሥልጣናቸው አነሱ።

https://p.dw.com/p/15oz1
epa03360878 Hundreds of supporters celebrate with posters showing Egypt's President Mohamed Morsi in front of the Presidential palace, in Cairo, Egypt, 12 August 2012. According to media reports on 12 August 2012, Egyptian President Morsi ordered the head of the army and defence minister, Field Marshal Tantawi and Chief of Staff Anan, into retirement and cancelled a constitution issued by the military restricting presidential powers. EPA/KHALED ELFIQI
በካይሮ የሙርሲን ውሳኔ በመደገፍ አደባባይ የወጣው ሕዝብምስል picture-alliance/dpa

ሙርሲ በታንታዊ ቦታ አብደል ፋታህ አል ሲሲን ሾመዋል። ግብፃዊው ፕሬዚደንት በትናንቱ ውሳኔአቸው የጦር ኃይሉ ባለፈው ሰኔ ወር የፕሬዚደንቱን ሥልጣን በሰፊው ለመቀነስ ሲል በሕገ መንግሥቱ ላይ አስቀምጦት የነበረውን አንቀጽ ሽረዋል። ፕሬዚደንት ሙርሲ ይህንኑ ያልተጠበቀ ውሳኔ በአሁኑ ጊዜ ለምን ወሰዱ? ውሳኔው ከግብፅ ሕዝብ በኩል ምን ዓይነት አስተያየት አስከትሎዋል?

ነቢዩ ሲራክ

አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሰ