1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፅ ፖለቲካዊ ዉዝግብ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 3 2004

ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ የሾሟቸዉ የግብፅ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ዳኞች፥ ግብፅን ከሐምሳ አመታት በላይ የገዛዉ ጦር ሐይልንና ከሰማንያ አራት-አመት በላይ በተቃዋሚነት የታገለዉን ሐይማኖታዊ ፓርቲ የሚወክሉትን ጠንካሮች ሽኩቻ እያጋግሙት ነዉ።

https://p.dw.com/p/15UvK
Machtkampf in Ägypten ARCHIV - HANDOUT - Feldmarschall Hussein Tantawi (l) sitzt während einer Abschlussfeier für Militärkadetten in Alexandria neben dem ägyptischen Präsidenten Mohammed Mursi (r) (Archivfoto vom 05.07.2012). Machtprobe in Kairo: Nach der Wiedereinsetzung des aufgelösten Parlaments durch Ägyptens Präsident Mursi will das Verfassungsgericht am Montag 09.07.2012 über dessen Dekret beraten. Bereits am Sonntagabend kam der oberste Militärrat zu einer Krisensitzung zusammen. Unter dem Vorsitz von Feldmarschall Hussein Tantawi wollten die Militärs «die Auswirkungen dieser Entscheidung» erörtern, berichtete die ägyptische Agentur Mena. Beschlüsse seien nicht gefasst worden, hieß es im britischen Sender BBC. EPA/SHERIEF ABDUL MONAM/EGYPTIAN PRESIDENCY HANDOUT EDITORIAL USE ONLY/NO SALES +++(c) dpa - Bildfunk+++
ማርሻሉና ፕሬዝዳንቱምስል picture-alliance/dpa

አዲሱ የግብፅ ፕሬዝዳት መሐመድ ሙርሲ ባለፈዉ ዕሁድ ባሳለፉት ትዕዛዝ መሠረት ባለፈዉ ሰኔ ተበትኖ የነበረዉ የግብፅ ምክር ቤት ዛሬ ተሰብስቧል።የግብፅ ጦር፥ ምክር ቤቱን የበተነዉ የሐገሪቱ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ምክር ቤቱን «ሕገ-ወጥ ነዉ» ብሎ በመወሰኑ ነበር።ፕሬዝዳት  ሙርሲ ምክር ቤቱ ዳግም እንዲሰየም ያሳለፉትን ዉሳኔም ወታደራዊዉ ምክር ቤትና ፍርድ ቤቱ ተቃዉመዉታል።የሙርሲ ዉሳኔ፥ የጦር ሐይሉና የሕገ-መንግሥታዊዉ ፍርድ ቤት ተቃዉሞ ወትሮም ያልተረጋጋዉን የግብፅን ፖለቲካዊ ቀዉስ እንዳያባብሰዉ አስግቷል።ነጋሽ መሐመድ ሐንስ-ሚሻኤል ኤሕል ከካይሮ በዘገበዉ ላይ ተመስርቶ የግብፅን ዉዝግብ ባጭሩ ይቃኛል።


የፕሬዝዳት መሐመድ ሙርሲ አዋጅ፥ቃል አቀባያቸዉ ባለፈዉ ዕሁድ እንዳነበበዉ።«ፕሬዝዳንቱ ባሳለፉት ዉሳኔ መሠረት፥-አንደኛ፥-ባለፈዉ ሰኔ አስራ-አምስት ምክር ቤቱ እንዲበተን የተላለፈዉ ዉሳኔ ተሽሯል።ሁለተኛ፥-የተመረጠዉ ምክር ቤት መጋቢት ሰላሳ፥ ሁለት ሺሕ አስራ-አንድ በፀደቀዉ ሕገ-መንግሥት መሠረት ተሰይሞ ሐላፊነቱን መወጣት አለበት።ሰወስተኛ፥-ሕዝቡ አዲስ ሕገ-መንግሥት ባፀደቀ በስልሳ ቀናት ዉስጥ የአዲስ ምክር ቤት አባላት ምርጫ ይደረጋል።»


በዚሕ አዋጅ መሠረት የግብፅ ሕግ-መምሪያ ምክር ቤት እንደራሴዎች ዛሬ ተሰበሰቡ።እንደራሴዎቹ ባጠገቡ እያለፉ ከትልቁ አዳራሽ ሲገቡ ያየዉ ባለ ኪዮስክ «እስካሁን ሠላም ነዉ» አለዉ ኪዮስኩ አጠገብ ቆሞ የእንደራሴዎቹን መሰብሰብ ለሚከታተለዉ ጋዜጠኛ «ነገ ግን እንደ ዛሬ አይቀጥልም።»

በርግጥም በአብዛኛዉ የሙስሊም ወንድማማቾች አባላት የሆኑት እንደራሴዎች የፕሬዝዳንታቸዉን ትዕዛዝ አክብረዉ ተራ-በተራ ከምክር ቤቱ አዳራሽ ሲገቡ የተተናኮላቸዉ ሐይል የለም።

የግብፅ ጦር ሐይል ጠቅላይ ምክር ቤት አዛዥ ፊልድ ማርሻል መሐመድ ሁሴይን ተንታዊና ፕሬዝዳንት ዶክተር ኢንጂነር መሐመድ ሙርሲ አዋጁ በወጣ ማግስት ትናንት እንደ ጥሩ ወዳጅ ጎን ለጎን ተቀምጦ ወታደራዊ ትርዒት ሲመለከቱ ያያቸዉ የዉጪ ታዛቢ በጣሙን አፍሪቃ-አረቡ በግብፆች መቻቻል ትንሽም ቢሆን መቅናቱ አልቀረም።

አብዛኛዉ ግብፃዊ ግን ልክ እንደ ባለኪዮስኩ ሁለቱ ግዙፎቹ የገጠሙትን ሽኩቻ መጨረሻ ለማየት-እንደ ጓጓ፥ እንደሰጋ ዛሬን አመሸ።በሕዝብ አመፅ ከሥልጣን የተወገዱት ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ የሾሟቸዉ የግብፅ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ዳኞች፥ ግብፅን ከሐምሳ አመታት በላይ የገዛዉ ጦር ሐይልንና ከሰማንያ አራት-አመት በላይ በተቃዋሚነት የታገለዉን ሐይማኖታዊ ፓርቲ የሚወክሉትን ጠንካሮች ሽኩቻ እያጋግሙት ነዉ።

ፍርድ ቤቱ የሙርሲን ፕሬዝዳንታዊ አዋጅ ትናንት ዉድቅ አድርጎታል።የፍርድ ቤቱ ዳኛ ኢብራሒም ደርዊሽ ጦሩ የፕሬዝዳንቱን አዋጅ ለመቀልበስ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።
                   
«ዉሳኔዉ የወታደራዊዉን ምክር ቤት ሥልጣን የሚጋፋና ምክር ቤቱን የሚቃረን ነዉ።ምክንያቱም ሕግ የማስከበሩ ሕገ-መንግሥታዊ ሐላፊነት የወታደራዊ ምክር ቤት ነዉ።ሥለዚሕ ወታደራዊዉ ምክር ቤት ሕልዉናዉንና ሥልጣኑን ማስከበር አለበት።ከሁሉም በላይ ዉሳኔዉ የግብፅ ሕግን የሚዳፈር ነዉ።ወታደራዊዉ ምክር ቤትና የግብፅ ሕግ ጥበቃ ካልተደረገላቸዉ ሕልዉናቸዉን ያጣሉ።»

ወታደራዊዉ ምክር ቤት ትናንት ባስቸኳይ ተሰብስቦ ከተነጋገረ በሕዋላ በቃል አቀባዩ በኩል የፕሬዝዳንቱን አዋጅ እንደማይቀበለዉ አስታዉቋል።መግጫዉ ግን የተፈራዉን ያክል ጠንካራ አልነበረም።የጄኔራሎቹን ልብ-ግን የሚያዉቅ ቀርቶ የሚገምትም ማግኘት ከባድ ነዉ።

Egypt's new President Mohamed Mursi (C) and Field Marshal Mohamed Tantawi (5th L), head of Egypt's ruling Supreme Council of the Armed Forces (SCAF), pose for a picture during a ceremony where the military handed over power to Mursi at a military base in Hikstep, east of Cairo, June 30, 2012. Mursi was sworn in on Saturday as Egypt's first Islamist, civilian and freely elected president, reaping the fruits of last year's revolt against Hosni Mubarak, although the military remains determined to call the shots. The military council that took over after Mubarak's overthrow on February 11, 2011, formally handed power to Mursi later in an elaborate ceremony at the desert army base outside Cairo. REUTERS/Mohamed Abd El Moaty/Egyptian Presidency/Handout (EGYPT - Tags: POLITICS ELECTIONS MILITARY) FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS
ፕሬዝዳንቱና ጦሩምስል Reuters
Egypt's new President Mohamed Mursi is pictured before his speech at Cairo University June 30, 2012. Mursi said on Saturday the military that took charge when Hosni Mubarak was overthrown last year had kept its promise to hand over power, speaking at a ceremony to mark the formal transfer of authority. REUTERS/Stringer (EGYPT - Tags: POLITICS ELECTIONS)
ፕሬዝዳንቱምስል Reuters

ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ                     









 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ