1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጎርጎረሳዉያኑ 11.11.2011 አ.ም እና የምዕራባዉያኑ እምነት

ሐሙስ፣ ኅዳር 7 2004

ባለፈዉ ሳምንት አርብ የጎርጎረሳዉያኑ 11.11.2011 አ.ም በዚህ በምዕራባዉያኑ ዘንድ ቀኑ ገድ ይለናል ብለዉ እድልናቸዉን ሲጠብቁ፣ በሌሎች ደግሞ አለም መጥፍያዋ ይሆን ብለዉ ያመኑ ጥቂት አልነበሩም።

https://p.dw.com/p/Rx2E
ሙሽሮች በጎርጎረሳዉያኑ 11.11.2011 አ.ምምስል dapd

በሕብረሰብ ጥናት ማለት ፎክሎር ስር አገረ ሰባዊ ልማድን እና እምነትን ተከትሎ ሕብረተሰብ የሆነ ነገርን ይዞ መልካም እድል ያመጣልኛል ወይም ገደቢስ ያደርገኛል ብሎ የሚያምንበት ድርጊት ምልኪ ይሰኛል። ባለፈዉ ሳምንት አርብ ይሄዉ የቀን የወር የዓመት ቁጥር አስራ አንድ አስራ አንድን ያዘ በመሆኑ ብቻ በጀርመን በርካቶች በትዳር ተሳስረዋል። ቀኑ በተለይ የሠመረ ትዳር እንዲያደርግላቸዉ በመመኝት። በዚህ ቀን ዓለም ትጠፋለች ብለዉ የሰጉም ጥቂቶች አልነበሩም፣ ሌሎች በዚህ ቀን ሥራ ከመሄድ ወይም የሆነ ነገር ከማድረግ የተቆጠቡም አሉ፣ ምናልባ ቀኑ ባይቀናኝስ በማለት። ብቻ የዛሬ ሳምንት አርብ በዚሁ እለት በጀርመን በርካቶች ሲጋቡ በድርቡ ካርኔቫል ማለት የጎዳና ድግሳቸዉን ሲጨፍሩ ቢራ ሲጠጡ ሲደሰቱ ከዋሉት በቀር የተከሰተ ክፉ ነገር አልነበረም፣ ግን ብቻ በዝያ እለት የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ዩክሪይን ኪይቭ በሚቀጥለዉ ዓመት ለሚደረገዉ የአዉሮጳ እግር ኳስ ጨዋታ ዉድድር አዲስ ስቴድዮም ለመመረቅ ከዩክሪኑ ብሄራዊ ቡድን ኪይቭ ላይ ባደረገዉ ጨዋታዉ ሶስት ለዜሮ ተመርቶ ባለቀ ሰአት ሶስት ግብን አስቆጥሮ በመለያየቱ ምናልባት ቀኑ ገድ አላለዉም ሰኔና ሰኞ ገጥሞበት ነበር ተብሎ በብዙሃን መገናኛ ተቀልዶበታል። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ


ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ