1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚኒሥትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋዜጣዊ መግለጫ

ሰኞ፣ ጥር 1 2009

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒሥትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የአገሪቱ የመኸር ምርት በ12 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ተናገሩ።

https://p.dw.com/p/2VXDG
Äthiopien Ministerpräsident Hailemariam Desalegn
ምስል Getty Images

Q&A PM HD Press Conference - MP3-Stereo

ጠቅላይ ሚኒሥትሩ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሳቢያ የፋብሪካዎች የምርት አልቀነሰም ሲሉም ተናግረዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ገቢራዊ ከመደረጉ በፊት  26 ፋብሪካዎች እና የአበባ እርሻዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒሥትሩ በሁለት ወራት ውስጥ ወደ ሥራ እንዲመለሱ መደረጉንም ገልጠዋል። ጠቅላይ ሚኒሥትር ኃይለማርያም በአገሪቱ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ኹከት ተቀይሮ በፋብሪካዎች እና የአበባ እርሻዎች ላይ በተፈጸመው ጥፋት የደረሰው ኪሳራ ወደ 450 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው ሲሉም ተደምጠዋል። 
በጋዜጣዊ መግለጫው የውጭ ንግዱ «ከሞላ ጎደል ከአምናው ጋር ተመሳሳይ» መሆኑን፤ የቱሪዝም ዘርፉ በሒደት ወደ ነበረበት እየተመለሰ መሔዱን ጠቅላይ ሚኒሥትሩ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚሥትሩ ጋዜጣዊ መግለጫውን ማለዳ በአማርኛ ከሰዓት በኋላ ደግሞ ለውጭ መገናኛ ብዙኃን በእንግሊዘኛ ሰጥተዋል። የአዲስ አበባው የዶይቼ ቬለ ወኪል ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የከሰዓት በኋላውን ታድሞ ነበር። 


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

 
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ