1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ ኃይለ ማርያም መነሳት እና ፋይዳው

ሐሙስ፣ የካቲት 8 2010

ገዢው ግንባር ኢሕአዴግ በአገሪቱ የታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የማሻሻያ እርምጃዎች እንደሚወስድ ቃል ሲገባ ቆይቷል። የአገሪቱን መረጋጋት ለመመለስ የጠቅላይ ምኒስትሩ ከስልጣን መልቀቅ ምን ፋይዳ ይኖረዋል?

https://p.dw.com/p/2sm3J
Äthiopien Ministerpräsident Hailemariam Desalegn kündigt Rücktritt an
ምስል picture-alliance/AP Photo

ማን ይመረጥ ይሆን?

ጠቅላይ ምኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በስልጣን በቆዩባቸው አመታት ኢትዮጵያ በተቃውሞ ስትታመስ ቆይታለች። በርካቶች ሞተዋል፤ ታስረዋልም። ገዢው ግንባር ኢሕአዴግ በአገሪቱ የታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የማሻሻያ እርምጃዎች እንደሚወስድ ቃል ሲገባ ቆይቷል። አባል ድርጅቶቹ እርስ በርስ መተማመናቸው ጎድሎ እንደነበር ሊቃነ-መናብርቱ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የአገሪቱን መረጋጋት ለመመለስ  የጠቅላይ ምኒስትሩ ከስልጣን መልቀቅ ምን ፋይዳ ይኖረዋል? የፖለቲካ ተንታኝ ቻላቸው ታደሰን እሸቴ በቀለ በስልክ አነጋግሯቸዋል። የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያዳምጡ።