1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም እና የምሁራን ውይይት

እሑድ፣ መጋቢት 18 2008

አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ሥልጣን ከያዙ ሦስት ዓመት ተኩል ያለፋቸው አቶ ኃይለማርያም በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ምሁራንን ለማወያየት ዘግይተዋል ሲሉ ሌሎች ደግሞ ቢዘግይም መካሄዱ በራሱ ጥሩ ነው ይላሉ ።

https://p.dw.com/p/1IK3T
Äthiopien Ministerpräsident Hailemariam Desalegn
ምስል Getty Images

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም እና የምሁራን ውይይት

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ልዩ ልዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ጋር ያካሄዱት ውይይት አስፈላጊነትና ውይይቱ የተካሄደበት ወቅት እያነጋገረ ነው ። በውይይቱ የተወሰኑ ምሁራን ብቻ መሳተፋቸውም ጥያቄዎችን አስነስቷል ። አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ሥልጣን ከያዙ ሦስት ዓመት ተኩል ያለፋቸው አቶ ኃይለ ማርያም በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ምሁራንን ለማወያየት ዘግይተዋል ሲሉ ሌሎች ደግሞ ቢዘግይም መካሄዱ በራሱ ጥሩ ነው ይላሉ ። የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም እና የምሁራን ውይይት ፋይዳና አንድምታው የዛሬው እንወያይ ርዕስ ነው ። ሙሉውን ውይይት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ ።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ