1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ

ዓርብ፣ ጥር 24 2011

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል በኢትዮጵያ የተለዪዩ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶች አሳሳቢነት የዜጎች ሞት መፈናቀል እና የንብረት ውድመትን፣ ህገ ወጥነትን  ስርዓተ አልበኝነትን ለመከላከል እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚወሰዱ እርምጃዎች፣ ላይ ያተኮሩት ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/3CajV
Äthiopien Ministerpräsident Abiy Ahmed
ምስል DW/G. Giorgis

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ዛሬ በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደ ልዩ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ላተኮሩ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል በኢትዮጵያ የተለዪዩ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶች አሳሳቢነት የዜጎች ሞት መፈናቀል እና የንብረት ውድመትን፣ ህገ ወጥነትን  ስርዓተ አልበኝነትን ለመከላከል እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚወሰዱ እርምጃዎች፣ወደ ሀገር የተመለሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጉዳይ ፣በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች የሚነሱ የክልል ይገባናል ጥያቄዎች፣ ትጥቅ ማስፈታት እና ህገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ላይ ያተኮሩት ይገኙበታል። ሂደቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሰጡትን ማብራሪያ እና በማብራሪያቸው ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን አሰባስቦ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል። 

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ