1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋ የድርድር ሀሳብ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 11 2002

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ከማንኛውም የተቃዋሚ ፓርቲ ፡ ከግንቦት ሰባት ጋ ጭምር ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን ባለፈው ሳምንት ማስታወቃቸው ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/OpOi

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር እና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋ የመደራደር ሀሳባቸው

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከማንኛውም የተቃዋሚ ፓርቲ ፡ ከግንቦት ሰባት ጋ ጭምር ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን ባለፈው ሳምንት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚንስትር መለስ መንግስታቸው ከአል ኢታድ አል ኢዝላሚያ ጋ ተወያይቶ ሰላም መፍጠሩን ጠቅሰው፡ ከኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ኦ ኤን ኤል ኤፍ ዋነኛ ክንፍም ጋ ተመሳሳይ ድርድር መቀጠሉን ገልጸዋል። ድርድሩ መልካሙን ውጤት እንደሚያስገኝ ተስፋቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትሩ ድርድሩ የሚካሄደው ግን፡ ዓመጽ የሚያካሂዱትም ሆኑ ሌሎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሀገሪቱን ህገ መንግስት እና ህገ መንግስታዊውን ስርዓት ሲያከብሩ እና በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፈቃደኞች ሲሆኑ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል። ይህ አሁን የቀረበው የድርድር ሀሳብ መንግስት እስካሁን በግንቦት ሰባት አኳያ ይዞት የነበረውን አቋም ለውጦ ይሆን የሚለውን ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም። የአዲስ አበባ ወኪላችን ታደሰ እንግዳው የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል አነግግሮዋል።

Taddesse Engidaw

Aryam Abraha

Negash Mohammed