1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠፉት ከተሞች

ረቡዕ፣ ሐምሌ 1 2012

ከአዲስ አበባ ወደ ሐዋሳ በሚወስደዉ መንገድ ግራ ቀኝ በሚገኙ ከተሞች በተለይም ቡል ቡላ፣ አርሲ ነገሌ፣ እና ሻሸመኔ ከተሞች የደረሰዉ ጥፋት አካባቢዎቹን በቃኘዉ በስዩም ጌቱ አገላለፅ «ከተሞቹን የጦር ቀጠና አስመስሏቸዋል።»

https://p.dw.com/p/3ez5h
Äthiopien Unruhen in Shashemene
ምስል Privat

ቡል ቡላ፣ አርሲ ነጌላና ሻሻመኔ ወድመዋል

ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለበት ካለፈዉ ሳምንት ሰኞ ማታ ጀምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሥለሞቱት ሰዎች የሐገሪቱ ባለስልጣናት የሚናገሩት ቁጥር እርስበርሱ እየተጣረሰ ነዉ።ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ የመንግሥት ባለስልጣናት በሰጡት መግለጫ የሟቾቹ ቁጥር 166 መሆኑን አስታዉቀዉ ነበር።ትናንት ማታ ደግሞ የሟቾቹ ቁጥር ወደ 239 ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።የኦሮሚያ መስተዳድር ባለስልጣናት ዛሬ እንዳሉት ግን የሟቾቹ ቁጥር 158 ነዉ።የሟቾቹ ቁጥር ግራ እንዳጋባ ከአዲስ አበባ ወደ ሐዋሳ በሚወስደዉ መንገድ ግራ ቀኝ በሚገኙ ከተሞች በተለይም ቡል ቡላ፣ አርሲ ነገሌ፣ እና ሻሸመኔ ከተሞች የደረሰዉ ጥፋት አካባቢዎቹን በቃኘዉ በስዩም ጌቱ አገላለፅ «ከተሞቹን የጦር ቀጠና አስመስሏቸዋል።» ሆቴሎች፣መደብሮች፣ የንግድና የመኖሪያ ሕንፃዎች፣የፖሊስና ያስተዳደር ፅሕፈት ቤቶች፣ ትምሕርት ቤቶች መኪኖችና ቁሳቁሶች ነድደዋል።ተሰባብረዋል።ወድመዋልም።የኢትዮጵያ መንግስት ጥፋቱን ለማስቆም አልጣሩም ያላቸዉን  የሻሸመኔ ከንቲባንና የፀጥታ ኃላፊዉን አስሯል።ኢትዮጵያ ዛሬም እንደመሰንበቻዉ የኢንተርኔት አገልግሎት ዝግነዉ። «ባለና በየለም» መካከል ብርዥ ጥርዥ በሚለዉ የስልክ መስመር ስዩምን አነጋግሬዋለሁ።

ስዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ