1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚሩ በዓለ ሲመትና የኪነ-ጥበብ ሚና  

ሐሙስ፣ መጋቢት 26 2011

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጥበብ ጋር ያላቸዉን ቅርርብ ስልጣን ከያዙም በኋላ ከጥበቡ ጎራ አለመራቃቸዉን  ብዙዎች ይናገራሉ። ይኸዉም በተለያዩ መድረኮች ብቅ ሲሉ መታየታቸዉ፤ የኪነ-ጥበብ ሰዎችን ወደ ጽ/ ቤታቸዉ መጋበዛቸዉ እና መወያየታቸዉ ለጥበብ ያላቸዉን ቅርበት ብሎም የጥበብን ኃይል ምንነት ጠንቅቀዉ የተረዱ ለመሆኑ ምስክር ነዉም ይባልላቸዋል።

https://p.dw.com/p/3GGli
Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed Rückblick auf die einjährige Millennium Hall
ምስል Ethiopian Broadcasting Corporation

ኢትዮጵያዊነት አማራጭ የማይገኝለት ነዉ።

« ዛሬ ጠዋት አንድ ታክሲ ከጀርባዉ ጽፎ ያየሁት እስከዛሬ ካየኻቸዉ ጽሑፎች ሁሉ የተለየ ነዉ። እስከዛሬ ሳይ የነበረዉ እያየህ ንዳ፤ አትከተለኝ፤ ብትገጨኝ ዋ! ፤ ዛሬ ያየሁት ግን ለየት ያለ ነዉ። ይኸዉ ነጋ ሰዉ ፍለጋ ይላል። የልቡን ነዉ የተናገረዉ። »  

Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed Rückblick auf die einjährige Millennium Hall
ምስል Ethiopian Broadcasting Corporation

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ አንደኛ ዓመት በዓለ ሲመትን በማስመልከት አዲስ አበባ ሚሌኒየም አዳራሽ የተካሄደዉን «ከሚያዝያ እስከ ሚያዝያ» የተሰኘዉን ልዩ ዝግጅት መድረክ የመራዉ አንጋፋው የመድረክ ንጉስ አርቲስት ደበበ እሸቱ በመድረክ ላይ ከተናገራቸዉ የተወሰደ ነዉ።  ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት የለዉጥ ርምጃ አልፎ አልፎ ተቃዉሞ ባይለየዉም አሁንም ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ድጋፍ አልተለየዉም።  የጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለ ሲመት አንደኛ ዓመት በሚለኒየም አዳራሽ በይፋ በተከበረበት ወቅትም የኪነ-ጥበብ ሠዎች ያቀረቧቸዉ መነባንብ ሥነ-ግጥም፤ በባህላዊ የሙዚቃ መሳርያ የተዋዛ ዘፈን ይህንኑ ጠቋሚ ነዉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስልጣን ከመያዛቸዉ በፊት ለጥበብ ቅርብ እንደሆኑ ይታመናል። ዐብይ በብዕር ስም መጽሐፍ እንዳሳተሙም ይታወቃል።  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጥበብ ጋር ያላቸዉን ቅርርብ ስልጣን ከያዙም በኋላ ከጥበቡ ጎራ አለመራቃቸዉን ብዙዎች ይናገራሉ። ይኸዉም በተለያዩ መድረኮች ብቅ ሲሉ መታየታቸዉ፤ የኪነ-ጥበብ ሰዎችን ወደ ጽ/ ቤታቸዉ መጋበዛቸዉ እና መወያየታቸዉ ለጥበብ ያላቸዉን ቅርበት ብሎም የጥበብን ኃይል ምንነት ጠንቅቀዉ የተረዱ ለመሆኑ ምስክር ነዉም ይባልላቸዋል። መጋቢት 24 ማክሰኞ 2011ዓ.ም ምሽት አዲስ አበባ ሚሌኒየም አዳራሽ ላይ የተካሄደዉን ይፋዊ ዝግጅት የመራዉ አንጋፋዊ አርቲስት ደበበ እሸቱ እንደሚለዉ ከሆነ ደግሞ ሙዚቃ ቋንቋን ማወቅ አይጠይቅም ሁለተኛ ኢትዮጵያዊነት አማራጭ የማይገኝለት ነዉ ። ኢትዮጵያዊነትን ኢትዮጵያን ማንገስ ይኖርብናል።      

Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed Rückblick auf die einjährige Millennium Hall
ምስል Ethiopian Broadcasting Corporation

«የጠቅላይ ሚኒስትሩን የሥራ ሂደት ከመጀመርያ ጊዜ ጀምሮ ስንመለከት ፤ በተለያዩ ሞያ ክፍሎች የሚሰሩ ባለሞያዎችን አነጋግረዋል ። የኪነ-ጥበብ ሰዎችንም ለብቻቸዉ ሰብስበዉ በኪነ-ጥበብ ቋንቋ አነጋግረዋል። የምሕንድስናዉንም፤ የሕክምናዉንም፤ በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ባለሞያዎችን ሁሉ ጠርተዉ ሲያነጋግሩ ሰዉየዉ ያላቸዉ ብቃትና እዉቀት ሰፊ መሆኑን ያሳያል። ይህንንም ጉዳይ ያሳሰባቸዉ፤ አንደኛ ሙዚቃ ቋንቋ ማወቅ አይጠይቅም፤ ኢትዮጵያዊነት አማራጭ የማይገኝለት ነዉ። ልክ እንደ ሙዚቃዉ ህብር ያለዉ ነዉ። ሙዚቃን አዳምጠነዉ ቋንቋዉም ባይገባን በሙዚቃዎቹ ምት ስሜታችን ረክቶ ሊደነቅ የሚቻል ጥበብ ነዉ። በመድረኩ ግጥም ያቀረቡት ባለሞያዎች ልጆችም ቢሆኑ፤ ኢትዮጵያ እያለች ግጥምን ካቀረበችዉ ታዳጊ ልጅ ጀምሮ፤ ልጅትዋ ልክ እንደናትዋ ኢትዮጵያ ማለት የቻለችዉ ያመድረክ በመዘጋጀቱ ነዉ። የግጥምን ኃይልም አሳይታናለች። ሌሎችም በመድረኩ የቀረቡ ባለሞያዎችን እንደ መሃሙድ አሕመድ አለማየሁ እሸቴን ያየን እንደሆን ሕብረትን አሳይተዉናል። ሕብረት ያስፈልጋል፤ አንድ መሆን ያስፈልጋል፤ ኢትዮጵያ አደጋ ዉስጥ እንዳትገባ የሁላችንም ተሳትፎ ተሰባስቦ፤ እጅ ለእጅ ተያይዞ ጥቃቅኖቹን ነገሮች ወይም በየቦታዉ እነዚህን ብልጭ ብልጭ የሚሉ ችግሮችን ለጊዜዉ ተቻችለን እና ለማስወገድ እየተመካከርን ፤ ኢትዮጵያን መሰረትዋ ላይ እናስቀምጥ እና ከዝያ በኋላ ስለሚቀጥለዉ ጉዳይ መነጋገር እንችላለን።   ደራሲና ገጣሚ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ በበኩላቸዉ፤      

Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed Rückblick auf die einjährige Millennium Hall
ምስል Ethiopian Broadcasting Corporation
Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed Rückblick auf die einjährige Millennium Hall
ምስል Ethiopian Broadcasting Corporation

ብዙዎች የዘረፉትን አስመላሽ፣ ገድለው የጣሉትን አፈላላጊ ያፈናቀሉትን ዜጋ አስፋሪ ሆነዋል። ማህበረሰባችን የስነ ምግባር አረም ለማብቀል ተስማሚ ሆኗል። ሰው ሲቃጠል እና ተዘቅዝቆ ሲሰቀል ኳስ እንደሚያይ ተመልች ከቦ በሚመለከተው፣ በሩን ዘግቶ በሚታዘበው እና ያንን ዜና ሰምቶ ቤቱ ገብቶ ይተኛል ሲሉ በሚሌኒየሙ ዝግጅት ላይ ጹሑፍ ያቀረቡት ደራሲ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ የሥነ ምግባር እሴታችንን ልንፈትሽ ልናጠነክር እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሙሉዉን ጥንቅር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ