1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚንስትር መለስ ሞትና የታዋቂ ፖለቲከኞች አስተያየት፣

ረቡዕ፣ ነሐሴ 16 2004

በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ጉልህ ሚና የነበራቸው፤ እሥርና እንግልት የደረሰባቸው፣ አሁን ፤ በዩናይትድ እስቴትስ ፤ በሃርባርድ ዩንቨርስቲ፤ በትምህርትና ምርምር ላይ የሚገኙት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳና አቶ ስዬ አብርሃ በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጡ።

https://p.dw.com/p/15uco
ምስል Reuters

በአሁኑ ወቅት፣ ተቃዋሚም ደጋፊም ፣ ጌዜውን ፣ ለዴሞክራሲና ፍትኅ ግንባታ፣ ለበጎ ለውጥ ማምጫ አድርገው እንዲጠቀሙበትም  ጥያቄአቸውን  አቅርበዋል።  የዋሽንግተኑ ዘጋቢአችን ፣ አበበ ፈለቀ፣ ወ/ት  ብርቱካን፣ በጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሞት ምን እንደተሰማቸው ጠይቋቸው ሲመልሱ----

አበበ ፈለቀ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ