የጠ/ሚ መለስ ህልፈት እና የፓርቲዎች አስተያየት
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 15 2004ማስታወቂያ
በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱትም ስርዓተ ቀብሩ እስኪፈፀም ብሄራዊ ሃዘን ነዉ፤ ሰንደቅ ዓላማም ዝቅ ብሎ ይዉለበለባል። መካነ መቃብራቸዉ የት እንደሚሆን ግን አልተገለፀም። እንደዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ከሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስከሬን ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ገብቷል።
በጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ የዜና እረፍት ላይ የተለያዩ አካላት፤ የአቶ መለስ ሞት፤ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አመራር ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ እየሰጡ ነው።
ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያነጋገርናቸው፤ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል፣ የአንድነት ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ እና የምክር ቤት አባል-አቶ ግርማ ሰይፉ ፣ አቶ ሴኩ ቱሬ ጌታቸው ከህወሓት፣ በአሁኑ ሰዓት የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር -ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር -ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የሰጡን አስተያየቶችን ማድመጥ ይቻላል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ልደት አበበ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሀመድ