1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ ኃይለ ማርያም ጉብኝት በአዉሮጳ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 9 2005

አቶ ኃይለ ማርያም የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ሥልጣን ከያዙ ወዲሕ ለመጀሪያ ጊዜ በአዉሮጳ በሚያደርጉት ጉብኝት ነገ ብራስልስ-ቤልጅግ ዉስጥ ከሌሎች የአዉሮጳ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገርም ቀጠሮ አላቸዉ።በብራስልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን ሥለ ጉብኝቱ የሚያቀዉ እንደሌለ አንድ የኤምባሲዉ ባለሥልጣን አስታዉቀዋል

https://p.dw.com/p/18HVP
ምስል Getty Images

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሽትራስ ቡርግ-ፈረንሳይ ዉስጥ ከአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳት ከማርቲን ሹልትስ ጋር ዛሬ ተወያዩ።ሁለቱ ባለሥልጣናት ከመወያየታቸዉ በፊት ባገኘነዉ መረጃ መሠረት፥ በዉይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት፥ ይዞታ፥ የፕረስ ነፃነት እና የአፍሪቃ ቀንድ ሠላም ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።አቶ ኃይለ ማርያም የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ሥልጣን ከያዙ ወዲሕ ለመጀሪያ ጊዜ በአዉሮጳ በሚያደርጉት ጉብኝት ነገ ብራስልስ-ቤልጅግ ዉስጥ ከሌሎች የአዉሮጳ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገርም ቀጠሮ አላቸዉ።በብራስልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን ሥለ ጉብኝቱ የሚያቀዉ እንደሌለ አንድ የኤምባሲዉ ባለሥልጣን አስታዉቀዋል።የብራሥልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንጉሤ

ነጋሽ መሐመድ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ