የጠ/ሚ አብይ አስተዳደር አንድ መቶ ቀናት

አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:02 ደቂቃ
11.07.2018

የዲፕሎማሲ ስኬቶች ተመዝግበውበታል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ የአንድ መቶ ቀናት የሥራ ስኬቶችን የተመለከተ አጠቃላይ መግለጫ ሰጠ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ  ስልጣን ከተረከቡ ዛሬ 100 ቀን ሆናቸው። በዚሁ ጊዜ በወሰዷቸው በርካታ ርምጃዎች  ለምሳሌ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ታይተው የነበሩ ተቃውሞና ግጭቶች እንዲያበቁ በማድረግ ውስጣዊ መረጋጋት አስገኝተዋል፣  የፖለቲካ እስረኞች ተፈተዋል፣ የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቷል። ከዚሁ ባሻገርም በጠቅላይ ሚንስትሩ ከፍተኛ ጥረት በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረኮች ከተለያዩ ሀገራት ጋር ብዙ  የተሳካ ዲፕሎማሲያዊ ስራ የተሰራበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

 ከዚሁ መካከልም ላለፉት ሀያ ዓመታት ከጎረቤት ኤርትራ ጋር ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት ካላንዳች የውጭ ሸምጋይነት በራሳቸው በሁለቱ ሀራት ህዝቦች እና መሪዎች ፍላጎት መልሶ የታደሰበት የሰላም ስምምነት ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የደረሱትን ስምምነት ተግባራዊ በማድረጉ ረገድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለጹንም አቶ መለስ አክለው ተናግረዋል። በጋዜጣዊ ጉባኤው ሌሎችም ጉዳዮች መነሳታቸው ተገልጿል።አርያም ተክሌ/ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ተዛማጅ ዘገባዎች