የጠ/ሚ አብይ የም/ቤት ገለጻ እና የህዝብ አስተያየት

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:32
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:32 ደቂቃ
19.06.2018

«ብዙ ያልተለመዱ ነገሮች፣ ሀሳቦች የተሰሙበት ትልቅ ንግግር ነው።»

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ በምክር ቤት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰጡት ገለጻ ባለፉት ዓመታት ይሰማ ያልነበረው የኢትዮጵያዊነት ስሜት የጎላበት ነበር ሲሉ ብዙዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ከሁለት ሰዓት በላይ የቆየው የጠቅላይ ሚንስትሩ ማብራሪያ የህዝቡን ተስፋ በሚገባ የገለጸ፣ እንዲሁም፣ በህዝቡ ልብ እና አዕምሮ የሚመላለሱ ጥያቄዎችን መረዳታቸውን ያሳየ ሆኖ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ