1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጡረተኞች ቅሬታ በአዋሳ

ዓርብ፣ የካቲት 25 2003

በቀድሞ መንግስት በተለያዩ ወታደራዊ የሥልጣን እርከኖች ያገለገሉ በአዋሳ ከተማ የሚኖሩ አቤቱታ አቅራቢዎች ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ የጡረታ ክፍያ እንደታገደባቸው፤ የሚበሉት የሚጠጡት አጥተው ለችግር እንደተጋለጡ በምሬት ይገልጻሉ።

https://p.dw.com/p/R6Pq
ምስል AP

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአቤቱታ አቅራቢዎቹ ተወካይ፤ 350 የምንሆን ጡረተኞች ላለፉት ስምንት አመታት ጡረታ ታግዶብን ከነቤተሰባችን አደጋ ውስጥ ነን ብለዋል።ከልጅነታችን ጀምሮ ያጠራቀምነው የራሳችን ገንዘብ እንጂ ከመንግስት ካዝና እንዲከፈለን አልጠየቀንም ያሉት አቤቱታ አቅራቢዎች በወንጀል ተጠይቀን ተለቀናል። መንግስትም የጡረታ አዋጁን ስላሻሻለ ሊታገድብን አይገባም ሲሉ ይገልጻሉ። አቶ አዳነ ደበበ በማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን የደቡብ ሪጅን የመዋጮ ገቢና አስተባባሪ ውሳኔ ክፍያ የሥራ ሂደት ባለቤት የሚሉት ከ20 ዓመት በታች ያገለገሉና 3 ዓመት በእስር የቆዩትን አዋጁ አያካትትም ነው።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ