1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጣልያን የፖለቲካ ቀዉስ 

ዓርብ፣ ነሐሴ 17 2011

የኢጣሊያዉ ጠቅላይ ሚንስትር  ጁሴፔ ኮንቴ  ከሥልጣን መልቀቅ የሐገሪቱን ሕዝብ እብዙ ሥፍራ ከፍሎ እያነጋገረ ነዉ።ኢጣሊያዉያን በጠቅላይ ሚንስትራቸዉ ሥልጣን መልቀቅ ባንድ  በኩል ግልግል፤ በሌላ ወገን ሥጋት እንዲሁም እፍረት እንደተሰማቸው እየገለጹ ነው።

https://p.dw.com/p/3OOtD
Italien Premierminister Giuseppe Conte im Oberhaus
ምስል picture-alliance/AP Photo/G. Borgia

ፓርቲዎቹ ካልተስማሙ ብሔራዊ ምርጫ ይካሄዳል

ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ የኢጣሊያን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ማቲዮ ሳልቪኒ የገዢውን ጥምረት አፍረክረከዋል፤ የሀገሪቱንም ኢኮኖሚ ለአደጋ አጋልጠዋል ሲሉ ወርፈዋቸዋል። ኮንቴ ባለፈዉ ማክሰኞ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ ለምክር ቤቱ ሲናገሩ፣ በተጣማሪነት የሚሠሩት የቀኝ ክንፍ ሊግ እና የአምስት ኮከብ እንቅስቃሴ የተባለው ፓርቲን ትስስር የሚያናጋ ርምጃ ወስደዋል በሚል ሳልቪኒን ከሰዋል። ኢጣልያ ዉስጥ  መንግሥት ባጭር ጊዜ ዉስጥ ስልጣን መልቀቅ እንደ ልማድ የሚታይ ነዉ።የሮሙ ዘጋብያችን ተኽለግዚ ገብረየሱስ እንደሚለዉ የጣልያኑ ፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ በመጪዉ ሳምንት ሁለቱን ትልልቅ ፓርቲዎች መሪዎች ጠርተዉ ያነጋግራሉ፤ ፓርቲዎቹ ጥምር መንግሥት ለመመስረት ካልወሰኑ ግን፤ ብሔራዊ ምርጫ ይካሄዳል።

ተኽለዝጊ ገብረየሱስ
አዜብ ታደሰ