1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶክተር አሚር መግለጫ

ዓርብ፣ ግንቦት 2 2011

የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ  ያልተመለሱት ቀሪ ጥያቄዎችም በሂደት የሚፈቱ ናቸው ብለዋል፡፡ የህክምና ተማሪዎች ማህበር ግን በሳምንቱ መጀመሪያ ለ DW እንዳለው አብዛኞቹ ጥያቄዎቻችን አልተፈቱም ሰላማዊው ትግላችንም ይቀጥላል ሲል አስጠንቅቆ ነበር፡፡

https://p.dw.com/p/3IIWV
Äthiopischer Gesundheitsminister Amir Aman
ምስል DW/S. Muche

የዶክተር አሚር መግለጫ

 
የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር የተለማማጅም ይሁን አጠቃላይ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተዋል አለ። የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ  ያልተመለሱት ቀሪ ጥያቄዎችም በሂደት የሚፈቱ ናቸው ብለዋል፡፡ የህክምና ተማሪዎች ማህበር ግን በሳምንቱ መጀመሪያ ለ DW አብዛኞቹ ጥያቄዎቻችን አልተፈቱም ሰላማዊው ትግላችንም ይቀጥላል ሲል አስጠንቅቆ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ሃገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጤና ባለሞያ የምትፈልግ ቢሆንም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ወደ ህክምና ትምህርት የሚገቡ ተማሪዎችን ቁጥር በመቀነስ የትምህርት ተቋማቱ የማስተማር ብቃትና ጥራት እንዲጣጣም ለማድረግ ታስቧልም ብለዋል ሚኒስትሩ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ጋዜጣዊ መግለጫውን ተከታትሎ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ