1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃን የሚከላከል ረቂቅ ሕግ

ሰኞ፣ ኅዳር 1 2012

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ባሉት ሕጎች የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን መከላከል ስለማይቻል በማለት አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲመራ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/3SqMU
Logo No Hate Speech Movement

«ለምክር ቤት ተመርቷል»

 የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃዎች ስርጭት ለፖለቲካ መረጋጋት ፣ ለሀገራዊ አንድነትና ለሰብአዊ ክብር ጠንቅ ሆነዋል የሚለው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፤ መልካም እሴቶች እየተሸረሸሩ ለሀገር ስጋት በመደቀናቸው በዚህ ድርጊት በሚሳተፉት ማንኛውም የመገናኛ አውታሮች እና ግለሰቦች ላይ የወንጀል ተጠያቂነት እንዲያስከትልና ማኅበራዊ መገናኛዎችን የሚያስተዳድሩት ተቋማትም መሰል ችግር ፈጣሪ ክስተቶችን ከስርጭት ውጪ እንዲያደርጉ ግዴታ የሚጥል ነው በማለት ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ተናግረዋል።

ዶይቼ ቬለ / DW / ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጉባኤ ሊቀመንበር አቶ አምሃ መኮንን ሕጉ በገሃድ የሚስተዋለውን ችግር ይፈታል የሚል እምነት እንደሌላቸው ፣ ይልቁንም መንግሥት በግልና በክልል መንግሥታት በሚመሩ ዋና ዋና መገናኛ ብዙሃን ላይ እርምጃ እንዲወስድና ሕጉ በጸረ ሽብር ሕግ አተገባበር ላይ የታየው አይነት መሠረታዊ የመናገር ነጻነትን እንዳይገድብ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት መምህር የሆኑ አንድ ግለሰብ ደግሞ ጉዳዩ ብዙዎች ባለቤት የሆኑበት በመሆኑ የሚኒስትሮችም ይሁን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች ከመድረሱ በፊት ለህዝብ ውይይት ክፍት መደረግ ነበረበት ብለዋል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ