1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት

እሑድ፣ ሚያዝያ 13 2011

የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት ጉዳይ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የቅርብ ጊዜ መነጋገሪያ ከመሆን አልፎ በፍጥነት ረቂቅ አዋጅ ወጥቶበታል። የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል በሚል የወጣው ረቂቅ አዋጅ ምንነት እና አስፈላጊነት ምን ይመስላል?

https://p.dw.com/p/3H6PT
Logo FDRE Federal Attorney Äthiopien

ረቂቅ አዋጁ በአኹኑ ወቅት ያስፈልጋል?

የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት ጉዳይ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የቅርብ ጊዜ መነጋገሪያ ከመኾን አልፎ በፍጥነት ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶበታል። የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል በሚል የወጣው ረቂቅ አዋጅ ምንነት እና አስፈላጊነት ምን ይመስላል?

ረቂቅ አዋጁ፦ ቅዳሜ መጋቢት 28 ቀን፤ 2011 ዓ.ም በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ  የማኅበራዊ መገናኛ አውታር ገጾች በኩል ለውይይት ቀርቧል። የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፦ «ሰብዓዊ ክብርን የሚገረስሱ እና ሆን ተብሎ የሚሰራጩ ሃሰተኛ ንግግሮችን በሕግ መከልከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኝቱ» ነው ብሏል። «የጥላቻ ንግግርና የሃስተኛ መረጃ ስርጭት የሚያስከትሉት ግጭትና ጉዳት ለእኩልነት፣ ለሰላም፣ ለዲሞክራሲና ለሕዝቦች አንድነት ትልቅ ጠንቅ» መኾናቸውንም ረቂቁ አሳስቧል። «መሰረታዊ መብቶች ላይ የሚጣሉ ገደቦች በሕግ የተደነገጉ፣ በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ውስጥ ተቀባይነት ያለውን አላማ ለማስፈጸም የሚወጡና ተመጣጣኝ መሆን እንዳለባቸው በመገንዘብ፤ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55(1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል» በማለት የረቂቅ አዋጁ ዝርዝር ቀርቧል። ዶይቼ ቬለ DW በጉዳዩ ላይ ውይይት አካሂዷል። ሙሉ ውይይቱን ከድምፅ ማእቀፉ ያድምጡ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ