1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥራጥሬ ምርቴ በሩስያ ተዘረፈ ያለችዉ ዩክሬይን

ሰኞ፣ ሰኔ 27 2014

ዩክሬይን እህል ከሃገሬ ዘርፎ ወጥቶአል ያለችዉን የሩስያን መርከብ ጥቁር ባህር ዳርቻ ላይ ይዛ እየመረመረች እንደሆን ቱርክ ዛሬ ዐስታወቀች። በቱርክ የዩክሬይን አምባሳደር እንደተናገሩት «ዚቢክ ዞሊ» የተባለዉ እና የሩስያን ባንዲራ ያነገበዉ ግዙፉ የሩስያ የጭነት መርከብ፤ በቱርክ የጉምሩክ ባለሥልጣን ተቆጣጣሪዎች በቁጥጥር ስር ገብቶአል።

https://p.dw.com/p/4DeFh
Türkei | russische Frachtschiff Zhibek Zholy vor Karasu
ምስል Yoruk Isik/REUTERS

ዩክሬይን እህል ከሃገሬ ዘርፎ ወጥቶአል ያለችዉን የሩስያን መርከብ ጥቁር ባህር ዳርቻ ላይ ይዛ እየመረመረች እንደሆን ቱርክ ዛሬ አስታወቀች። በቱርክ የዩክሬይን አምባሳደር ትናንት እሁድ ምሽት እንደተናገሩት  «ዚቢክ ዞሊ» የተባለዉ እና የሩስያን ባንዲራ ያነገበዉ ግዙፉ የሩስያ የጭነት መርከብ፤ በቱርክ የጉምሩክ ባለሥልጣን ተቆጣጣሪዎች በቁጥጥር ስር ገብቶአል። ከዚህ ቀደም ሲል ዩክሬይን ሩስያ ያመረትኩትን እህል ሩስያ ዘርፋ በመርከብ ጭና ሄዳለች ስትል ቱርክ መርከቡን እንድትይዝ ተማፅና ነበር። መዲና ኪይቭ የሚገኘዉ የዩክሬይን የሩስያ መንግሥት ዩክሬይንን መዉረር ከጀመረ ካለፈዉ የካቲት ወር አንስቶ በቁጥጥር ከያዛቸዉ ከተሞች ያገኘዉን እህል ሁሉ ሰርቆ ጭኖ ወስዷል ሲል ይከሳል።  ከቱርክ በተሰማዉ ዜና ደግሞ በቁጥጥር ስር ያለችዉ የሩስያ መርከብ የጫነችዉ እህል ላይ እስካሁን የዩክሬይን ስለመሆኑ ምንም ማስረጃ አልተገኘም ተብሎአል። የዩክሬይን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሃገሪቱን የባህር ሃይል መረጃ ጠቅሶ ባወጣዉ መረጃ መሰረት «ዚቢክ ዞሊ» የተባለዉ የጭነት መርከብ በሩስያ ቁጥጥር ስር ከሚገኘዉ ከደቡባዊ ዩክሬይን ባርድያንስክ ወደብ 4,500 ቶን እህል ጭኖ ወጥቶአል።

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ