1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥበብ ፈርጦች ይታሰቡ!

ሐሙስ፣ ሰኔ 2 2003

በኪነጥበብ ሞያቸዉ የኢትዮጽያን ክብር እድገት ብልጽግና በመመኝት አዚመዉላታል፣ ብልጽግና እና እድገት በህብረት ተስማምቶ በመስራት ሊገኝ እንደሚችል፣ በኪነጥበብ ሞያቸዉ አስተምረዉበታል አስተጋብተዋልም!

https://p.dw.com/p/RREs
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

የአገር ባህሉ ፈርጥ የፉከራና የሽለላዉ አባት የመሲንቆዉ ጌታ የባህል ሙዚቃዉ አንባሳደር ይርጋ ዱባለ፣ በመሲንቆ ጭራ አገር አስከባሪ፣ በመረዋ ድምጹ ስሜት የሚያረካ፣ ስሜት የሚያነቃ፣ ጭንቀት የሚያስረሳ፣ አገር ተላላ ነዉ እያለ ዳመሉ ማሲንቆ ሲመታ ሲያቅራራ በቃሉ ነፍስ የሚዘራበት የፈራዉን ሁሉ፣፡የሚቀሰቅሰዉ የተኛዉን ሁሉ ! ተብሎላቸዋል፣ የሰማንያ አንድ አመቱ አዛዉንት ይርጋ ዱባለ በሰማንያ አንድ አመታቸዉ ከዚህ አመት ቢለዩንም ስራቸዉ ስማቸዉ ከመቃብር በላይ ዉሉአል። ሊቀ መኳስ ይርጋ ጉባለን በማሰብ የባህል ሙዚቃችን እንዲያብብ ለትዉልድም ታሪክን ባህልን ለማስተላለፍ ምን እየተደረገ ነዉ? በለቱ ቅንብራችን የምናየዉ ነዉ ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
ሸዋዪ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ