1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥንታዊ ቅርሳ ቅርሶች ህገ-ወጥ ንግድ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 20 2007
https://p.dw.com/p/1DeVP

የአሸባሪ ድርጅቶች በመካከለኛዉ ምሥራቅ የሚገኙ ጥንታዊና ታሪቃዊ ቅርሶችን በመዝረፍና በከፍተኛ ገንዘብ በማግኘት ላይ መሆናቸዉ ተመልክቶአል። ይህን ጥንታዊ ቅርስ ከሚገዙት ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርስ አድናቂዎች እና ሰብሳቢዎች መካከል ደግሞ ጀርመናዉያንም እንደሚገኙበት ተመልክቶአል። ይህ የተዘረፈ እቃ መሸጡና አሸባሪዎች እንዲጠቀሙበት የሆነበት ዋና ምክንያት ደግሞ በቅርስ ዝዉዉር ላይ ያለዉ ልል የሆነዉ የዓለም ዓቀፉ ህግ ነዉ፤ ሲሉ ምሁራን ያላቸዉን አስተያየት ይሰጣሉ። የዕለቱ ዝግጅታችን በመካከለኛዉ ምሥራቅ የእርስ በርስ ጦርነት በሚታይባቸዉ ሃገራት እየተሰረቀ ስለሚወጣዉ ጥንታዊና ታሪካ ቅርስ ዘገባ ይዞአል ።