1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጦር መሣሪያ ንግድ ቁጥጥር ውል

ረቡዕ፣ መጋቢት 25 2005

ድምፃቸውን ካቀቡት ውስጥ ዋነኛዎቹ የጦር መሣሪያ ነጋዲዎች ሩስያ ና ቻይና እንዲሁም የጦር መሣሪያ ገዥዎች ግብፅና ህንድ ይገኙበታል ። ውሉን ከደገፉት አንዷ ዋነኛዋ የጦር መሣሪያ ነጋዴ አሜሪካን ስትሆን በአሜሪካን ውሉ መፅደቁ አጠራጣሪ መሆኑ ከወዲሁ እየተነገረ ነው ።

https://p.dw.com/p/188sW
ምስል Timothy a. Clary/AFP/Getty Images

ለረዥም ጊዜ ሲከራክር የቆየውን የጦር መሣሪያ ሽያጭና ዝውውር ቁጥጥር ረቂቅ ውል የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት አፅድቋል ። ረቂቁ ከ193 አባል ሐገራት የ154 ቱን ድጋፍ ሲያገኝ 3 አገራት ተቃውመውታል ። 23 ደግሞ ድምፃቸውን አቅበዋል ። ድምፃቸውን ካቀቡት ውስጥ ዋነኛዎቹ የጦር መሣሪያ ነጋዲዎች ሩስያ ና ቻይና እንዲሁም የጦር መሣሪያ ገዥዎች ግብፅና ህንድ ይገኙበታል ። ውሉን ከደገፉት አንዷ ዋነኛዋ የጦር መሣሪያ ነጋዴ አሜሪካን ስትሆን በአሜሪካን ውሉ መፅደቁ አጠራጣሪ መሆኑ ከወዲሁ እየተነገረ ነው ። ታሪካዊ ስለ ተባለው ስለዚሁ ውል ምንነትና ተፈጻሚነት የዋሽንግተን ዲሲውን ዘጋቢያችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ