1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጫት ንግድና የኒውዮርኩ ብይን

ሰኞ፣ መጋቢት 21 2007

በዩናይትድ ስቴትስ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ፣ ከአፍሪቃዉ ቀንድ የመጡ ሶስት ግለሰቦች በጫት ንግድ ሳቢያ በወንጀለኝነት ተከሰዉ ከሁለት እስከ ሶስት ዓመት እስራት ተፈረደባቸዉ። ዐቃቤ ሕጉ እንዳሉት፣ ጫት ለብዙ የወንጀል ድርጊቶች የሚገፋፋ እጽ ነው።

https://p.dw.com/p/1Ezhl
Symbolbild Khat
ምስል AFP/Getty Images/Z. Abubeker

ባለፈው ሳምንት ማለቂያ ገደማ ላይ ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኒው ዮርክ ከተማ ታሪክ ፣ 3 የምሥራቃዊው አፍሪቃ ተወላጆች፤ የ 24 ዓመቱ ወጣት፣ ያደታ ወይም ሙራድ በክሪ እንዲሁም የ 32 ዓመት ጎልማሶች አህመድ አደምና በያን ዩሱፍ፣የተባሉት ፣ በጫት ንግድ ሳቢያ ከ 2 እስከ 3 ዓመት በእሥራት እንዲቀጡ ተበይኖባቸዋል ፤ ብይኑ የሚጸናው በሚመጣው ወር ነው ። ብሪታንያ ባለፈው ዓመት እርከን በእርከን፤ ከበድ ያሉ ቅጣቶች ተፈጻሚ እንደሚሆኑ ካስታወቀች ወዲህ ፣ እንሆ ኒውዮርክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰውን ርምጃ ወስዳለች። የተጠቀሱትን 3 ሰዎች በትክክል ፍርድ ቤት በምንድን ነው ጥፋተኞች ሆነው ያገኛቸው? የዋሽንግተን ዲ ሲ ውን ዘጋቢአችንን አነጋግረነዋል።

መክብብ ሸዋ

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ