1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ደረጀ ትዕዛዙ»

እሑድ፣ ታኅሣሥ 1 2010

ደረጀ ለህትመት ካበቃቸው መጻህፍት የመጀመሪያው የጳውሎስ ኞኞ የህይወት ታሪክ ነው።ደራሲ መባሉን ባይፈልግም ሁለት መጻህፍት ለአንባብያን አቅርቧል።የአንድ መፀሐፍ ዐርታዒም ነበር።

https://p.dw.com/p/2p3J1
Symbolbild Buch Bücher Lesen
ምስል Colourbox

ደረጀ ትዕዛዙ

ከጋዜጠኝነት ሥራው ጎን ለጎን ለህትመት ካበቃቸው ከነዚህ መጻህፍት አንዱ የጳውሎስ ኞኞ የህይወት ታሪክ ብዙ የተማረበት እና የረካበት ነው። ደረጀ ያደገው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ ሰፈር አዲስ አበባ ጦር ኃይሎች አካባቢ ነው። ከልጅነቱ አንስቶ የሚያውቀውን የጳውሎስ ኞኞን የህይወት ታሪክ ለመጻፍ የበቃውም በማስሚድያ ማሠልጠኛ ተቋም ተማሪ ሳለ በጳውሎስ ኞኞ ታሪክ ላያ ያተኮረ የመመረቂያ ጽሁፉ ከሠራ በኋላ መሆኑን ይናገራል። ታሪኩን ወደ መፀሀፍ ያሳደገው ከ10 ዓመት በኋላ ነበር ። እርሱ እንደሚለው ያኔ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መሥራቱ ሥራውን አቃንቶለታል።  ደረጀ በጳውሎስ ኞኞ የህይወት ታሪክ ብቻ ሳይገደብ ወደፊት የሌሎች ታዋቂ ኢትዮጵያውያንን ታሪክ ለአንባብያን የማቅረብ እቅድ አለው። የአንዳንዶቹንም መጻፍ ጀምሯል።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ