1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፈላሻ ሙራ የእስራኤል ጉዞ

ሐሙስ፣ ጥር 12 2003

ከብዙ ዓመታት ወዲህ ወደ እስራኤል ለመሄድ በመጠበቅ ላይ ከሚገኙት ፈላሻ ሙራ በመባል የሚታወቁት ቤተ እስራኤላውያን መካከል የመጀመሪያዎቹ ሶስት መቶ አርባ ሰሞኑን እስራኤል መግባታቸውን የእስራኤል የአይሁዳውያኑ ወኪል ድርጅት ቃል አቀባይ ማይክል ጃንኮሌቪትስ አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/QtxM
ምስል picture alliance/dpa

ወደ እስራኤል ለመጓዝ በኢትዮጵያ በመጠባበቅ ላይ ያሉት ስምንት ሺህ ቤተ እስራኤላውያንን በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ ለመውሰድ ዕቅድ እንዳለም ከመላ ዓለም ወደ እስራኤል ለመሄድ ለሚፈልጉ አይሁዳውያን ሁኔታዎችን የሚያመቻቸው የዚሁ ድርጅት ቃል አቀባይ አክለው ገልጸዋል። አርያም ተክሌ አነጋግራቸዋለች።

አርያም ተክሌ

ሒሩት መለሰ