1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዝደንት ማክሮ በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 3 2011

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮ ለጉብኝት ኢትዮጵያ ገብተዋል። በዛሬው ዕለትም ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮ በላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት ጉብኝት አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/3EtSi
Unesco Äthiopien - Ortodoxe Kirceh Lalibela
ምስል Getty Images/AFP/C. de Souza

ፕሬዝደንት ማክሮ በላሊበላ ጉብኝት አድርገዋል

 በጉብኝቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ-መሥተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ተገኝተዋል። ፈረንሳይ የከፋ ጉዳት ላይ ለሚገኙት ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት የዕድሳት ድጋፍ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል። ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ጉብኝት ያደርጋሉ። ከፕሬዝዳንቱ ጋር የተጓዘችው ሃይማኖት ጥሩነሕ ከአዲስ አበባ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅራለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

እሸቴ በቀለ