1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤማኑኤል ማክሮ በጀርመን 

ማክሰኞ፣ ግንቦት 8 2009

የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ኤማኑኤል ማክሮ የመጀመሪያ ብሔራዊ ጉብኝታቸውን ወደ ጀርመን አድርገው ከመራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ጋር ተገናኝተዋል።

https://p.dw.com/p/2d4Yb
Emmanuel Macron und Angela Merkel Berlin
ምስል Reuters/F.Bensch

«አፍሪቃውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከማይናገር ትውልድ ነው የመጣሁት።»

ፕሬዝዳንቱ በርሊን ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የጀርመኗ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከማክሮ ጋር ከመከሩ በኋላ በሰጡት መግለጫ ለሁለቱ አገራት ግንኙነት አዲስ ትንፋሽ ሊዘሩበት መስማማታቸውን ተናግረዋል። የአውሮጳ ኅብረትን ሊያጠናክሩም ማቀዳቸው ተሰምቷል። ፕሬዚዳንት ማርኮ በይፋ ስልጣን ከተረከቡ በኋላ መጀመሪያ የጎበኙት በርሊን-ጀርመንን መሆኑ ነዉ። ትናንት ከቀትር በኋላ በርሊን ሲገቡም ከፍተኛ ወታደራዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።ወደ ጀርመን በመምጣታቸዉ ከፍተና ኩራት ይሰማናል ሲሉም መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከአቀባበሉ ስነስርዓት በኋላ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል። « የመጀመርያዉን ጉዞዉን ወደ ጀርመን በተለይ ወደ በርሊን በማድረጎ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል። እንደሚመለከቱት እጅግ ብዙ ጋዜጠኞች ተሰብስበዋል ሥለ ጉዳዩ ላይ ለማወቅ ብዙ ጉጉት እንዳላቸዉ ያሳያል። ዛሬ በጋራ ለመስራት ሃሳቦችን ተለዋዉጠን ተስማምተናል። በርግጥ በመጀመርያ ፕሬዚደንቱ ሳገኛቸዉ ለዚህ ስልጣን ለመብቃት በምርጫዉ ዘመቻ ለሄዱበት  ጠንካራና የድፍረት መንገድ እንኳን ደስ ያሎት ብያለሁ።  

ይልማ ኃይለሚካኤል

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሃመድ