የፈጠራ ሥራዎች እና አይስአዲስ
ዓርብ፣ መጋቢት 20 2005ማስታወቂያ
አይስአዲስን የመሠረቱት አራት ወጣቶች ናቸው። ሥራም ከጀመሩ አንድ አመት ተኩል ሆኗቸዋል። ወጣቶቹ አይስአዲስን ለመጀመር የተነሳሱት በጀርመን አለም አቀፍ ትብብር በምህፃሩ GIZ አማካኝነት ነው። ከመሥራቾቹ አንዱ ማርቆስ ለማ ነው። ሌሎቹ የጀርመን፣የሲውዲን እና የሃንጋሪ ዜጎች ናቸው።
«ብዙ ወጣቶች እውን ማድረግ የሚፈልጉት ሀሳብ አላቸው ። ያ ሃሳብ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር እውን በማድረጉ ሂደት ላይ ድጋፍ እንሰጣቸዋለን» ይላል፤ ማርቆስ። አይስአዲስ ስለሚያበረታታቸው የፈጠራ ሥራዎች እና እንቅስቃሴ ይገልፅልናል።
ወደ አይስአዲስ የሚሄዱት ወጣቶችም ብዙ የፈጠራ ስራ የያዙ መሆናቸውን ማርቆስ ገልፆልናል። አይስአዲስ በአሁኑ ወቅት 500 አባላት እንዳሉት ድረገፁ ላይ ተፅፏል። አባል ለመሆን ምን ያስፈልጋል? መስፈርቱስ ምንድን ነው? ማርቆስ ያብራራል።
አይስአዲስ ስለሚያበረታታቸው የፈጠራ ሥራዎች እና እንቅስቃሴ ለመስማት ከፈለጉ
የዛሬውን የወጣቶች አለም ዝግጅት ያድምጡ።
ልደት አበበ
ነጋሽ መሐመድ