1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፊልም ሥራ በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ የካቲት 6 2007

አጥኚዉ እንደሚሉት የፊልም ሥራ ኢትዮጵያ ዉስጥ ረጅም ዘመን ቢያስቆጥርም ብዛቱም ሆነ ጥራቱ ናጄሪያ፤ ግብፅ፤ እና ጋናን ከመሳሰሉ ሐገራት ጋር ሲወዳደር ግን አነስተኛ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1EbOq
ምስል picture-alliance/ dpa

የኢትዮጵያ ዉስጥ የሚሠሩና የሚመረቱ ፊልሞች ቁጥርና ጥራት እያደገ መምጣቱን አንድ ብሪታንያዊ የፊልም ጥበብ ባለሚያ አስታወቁ። ለንደን ዩኒቨርሲ ባዘጋጀዉ ሥብሰባ ላይ ሥለ ኢትዮጵያ ፊልም ያደረጉትን ጥናት ያቀረቡት ማይክል ቶማስ እንደሚሉት ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ1997 የተሠሩት ፊልሞች 10 ብቻ ነበሩ። ከ1998 እስካሁን በተቆጠሩት ሰባት አመታት ግን ከአምስት መቶ በላይ ፊልም ተሠርቷል። ያም ሆኖ አጥኚዉ እንደሚሉት የፊልም ሥራ ኢትዮጵያ ዉስጥ ረጅም ዘመን ቢያስቆጥርም ብዛቱም ሆነ ጥራቱ ናጄሪያ፤ ግብፅ፤ እና ጋናን ከመሳሰሉ ሐገራት ጋር ሲወዳደር ግን አነስተኛ ነዉ። የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ