1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፋይናንስ ዘርፉና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን

ሰኞ፣ የካቲት 18 2011

የኢትዮጵያ መንግሥት የፋይናንስ ዘርፉን የዉጭ ዜግነት ላላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ክፍት ለማድረግ ማሰቡ ጥሩ ዉሳኔ መሆኑን አንድ የምጣኔ ኃብት ባለሞያ ለ«DW» ገለፁ ። የዘርፉ መከፈት ለሃገሪቱ ልማት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለዉም ባለሞያዉ ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/3E3j6
Äthiopien Addis Abeba | Nationalbank
ምስል DW/H. Melesse

ዲያስፖራዉ በፋይናንስ ዘርፉ እንዲሳተፍ እንደሚያበረታታ ነዉ

ኢትዮጵያ በፖለቲካዉ በኩል እያስመዘገበችዉ ከምትገኘዉ ለዉጥ ጎን ለጎን ምጣኔ ኃብቱንም ለማነቃቃት የምታደርገዉ እንቅስቃሴ ወሳኝ መሆኑን የመስኩ ባለሞያዎች ይናገራሉ። በሃገሪቱ ዉስጥ ከሚገኙ የፋይናንስ ዘርፎች የዉጭ ዜግነትን ያገኙ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን እንዳይሳተፉ የሚያግደዉን ሕግ ኢትዮጵያ እንደምታሻሽል በመግለፅ ላይ ትገኛለች። ረቂቅ ሕጉ ከተሻሻለ በዉጭ ሃገራት የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ « ዲያስፖራ» በፋይናንስ ዘርፉ እንዲሳተፍ ያበረታታል ተብሎአል።

   
መክብብ ሸዋ 


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ