1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ በድጋሚ ሊሻሻል ነው

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 12 2011

ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ሰበር ሰሚ ችሎት የሚቀርቡ ጉዳዮች በየአመቱ በመጨመራቸው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጫና ውስጥ መግባቱን የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ ተናገሩ፡፡

https://p.dw.com/p/3H98U
Äthiopien | Änderung der Proklamationsdiskussion der Bundesgerichte
ምስል DW/S. Murchi

ፍርድ ቤቱ በሃገር አቀፍ ደረጃ ጠቀሜታ ላላቸው ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት የዜጎችን መሰረታዊ መብቶች በማስጠበቅ መሪ የህግ ትርጉም መስጠት ሲጠበቅበት በብዙ ጉዳዮች ተጨናንቆ አላማውን እንዳይስት በተደጋጋሚ ማሻሻያ የተደረገለት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 ከህዳር 28 /2011 ጀምሮ ማሻሻያ ሲደረግለት ቆይቷል፡፡ አዋጁ በቀጣይ አንድ ወር ውስጥ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቦ ሲጸድቅ የዳኝነት ስርአትና የፍርድ ቤቶች መዋቅር ይሻሻላል፣ ህገመንግስታዊ የዳኝነት ነጻነትም እውን እንዲሆን ይረዳል ተብሏል፡፡አዋጁ ላለፉት 20 አመታት በስራ ላይ የነበረ ቢሆንም ብዙ ችግሮች እንደነበሩበት ተነግሯል፡፡ ልምዱ ከአሜሪካ እንደተወሰደ የተነገረለት ይህ የተሻሻለው አዋጅ በሰበር ሰሚ ችሎት ውስን ሃገራዊ ጉዳዮች ብቻ እንዲታዩ፣ በመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች እስከ 500 ሽህ ብር ብቻ የሚታዩ የነበሩ የፍትሃብሄር ጉዳዮች እስከ 20 ሚሊዮን ብር እንዲያድግ እና ፍርድ ቤቶች አሁን ካለው የ 1 ዳኛ ችሎት ወደ 3 እንዲያድጉ የሚሉ ሃሳቦችን በማንሳት አወያይቷል፡፡

Äthiopien | Änderung der Proklamationsdiskussion der Bundesgerichte
ምስል DW/S. Murchi

ሰለሞን ሙጬ

ልደት አበበ