1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፍትኃዊ ዳኝነት እጦት ፈተና

ሰኞ፣ ጥር 20 2011

የኢትዮጵያ የፍትኅ ተቋማት ከፍርድ በፊት ተከሳሾች ነፃ እንደሆኑ በማየት ረገድ ጉድለት እንዳለባቸው የሕግ ባለሙያዎች ተናገሩ። ከሳሽ አቃቤ-ሕግ እና ተከሳሾችን እኩል የማየት ችግር እንደሚታይም ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3CKxQ
Äthiopien Workshop der Universität in Addis Abeba
ምስል DW/Y. Geberegziabher

የፍትኃዊ ዳኝነት እጦት ፈተና

የኢትዮጵያ የፍትኅ ተቋማት ከፍርድ በፊት ተከሳሾች ነፃ እንደሆኑ በማየት ረገድ ጉድለት እንዳለባቸው የሕግ ባለሙያዎች ተናገሩ። አቃቤ-ሕግ እና ተከሳሾችን እኩል የማየት ችግር እንደሚታይም ገልጸዋል። ባለሙያዎቹ ይኸን ያሉት በአዲስ አበባ በፍትኃዊ ዳኝነት ላይ በመከረ ስብሰባ ላይ ነው። ውይይቱን ያዘጋጁት የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብት የተባለ አገር በቀል ድርጅት እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብት ማዕከል ናቸው። የሕግ ባለሙያዎች ፤ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፤ ዳኞች እና አቃብያነ-ሕግ ተሳትፈውበታል። 
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
አዜብ ታደሰ