1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፎቶ ስብስቦቿን በኒው ዮርክ የምታስገመግመው ወጣት

Lidet Abebeዓርብ፣ መጋቢት 16 2008

በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ኒው ዮርክ ውስጥ ከ150 በላይ ፎቶ አንሺዎች የሚካፈሉበት እና ስራዎቻቸው የሚተችበት የሁለት ቀናት ዝግጅት ይካሄዳል። በእንግድነት ከተጋበዙ ፎቶ አንሺዎች መካከል በአዲስ አበባ ከተማ የምትኖረው ፤ ወጣት እየሩሳሌም አዱኛ አንዷ ናት።

https://p.dw.com/p/1IJWI
ምስል Eyerusalem Adugna

የፎቶ ስብስቦቿን በኒው ዮርክ የምታስገመግመው ወጣት

ከተለያየ ሀገር የተወዳደሩ ፎቶ አንሺዎች ተገኝተው ስራዎቻቸውን በተለያዩ ባለሙያዎች የሚያስገመግሙበት አራተኛው ዓመታዊ የኒው ዮርክ «ፖርትፎሊዮ ሪቪው» መጋቢት 24 እና 25 ቀን 2008ዓም ኒው ዮርክ ላይ ይካሄዳል። አዘጋጁ ደግሞ የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ነው።
በዚህ ዝግጅት የፎቶ ስራዎቻቸውን ለማስገምገም እድሜያቸው ከ 21 ዓመት በላይ የሆኑ ፎቶ አንሺዎች ተወዳድረዋል። የ 22 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ኢየሩሳሌም አዱኛ ከተመራጮቹ አንዷ ናት። ወጣቷ በስድስት ቀናት የኒው ዮርክ ቆይታዋ ፎቶዎቿን የምታቀርብበት ሌላ መድረክ ወይም ወጪዎቿን ለመሸፈን የሚተባበሯት አካል ለማፈላለግ ትጥራለች። ወጣቷ ፎቶ ማንሳት ከጀመረች ሶስት አመት ጊዜ የሆናት ሲሆን፤ አጠናክራ ከጀመረች ገና አንድ ዓመት ተኩል ሆናት። ይህንንም የተማረችውም፤ አጫጭር ኮርሶች በመውሰድ እንደሆነ ትናገራለች። ሶስት የተለያዩ የሙያ ዘርፎችን የዳሰሰችው እየሩሳሌም በመጨረሻም ወደ ፎቶ ማንሳት አድልታለች። ወደፊትም በዚህ የመቀጠል ዓላማ ነው ያላት።
ኢየሩሳሌም አዱኛ ኒው ዮርክ ስለምታቀርባቸው የፎቶ ስብስቦቿ እና ሥራዋ ያጫወተችንን በድምጽ ያገኙታል።


ልደት አበበ
ሂሩት መለሰ