1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፔጊዳ ሰልፈኞች እና የጀርመን ገፅታ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 14 2007

«የምዕራብ ፀረ-እስልምና የአውሮፓ አርበኞች» በጀርመንኛ ምህፃሩ ፔጊዳ የተሰኘዉ ኅብረት ፤ የጀርመን ዋና የመነጋገሪያ ርዕስ ከሆነ ሰነበተ። ህብረቱ ተቃውሞ ቢገጥመውም ትናንት 10ኛውን የተቃውሞ ሰልፍ በድሬስድን ከተማ አካሂዷል።

https://p.dw.com/p/1E9IZ
Pegida-Kundgebung in Dresden
ምስል Reuters/Hannibal Hanschke

የሰልፈኛው ቁጥር ከባለፈው ሳንምት በ2500 ጨምሮ17 500 ደርሷል። ራሳቸውን የቀኝ ፅንፈኞች ብለው ባይጠሩም፤ ለበርካታ ታዛቢዎች ልዩነቱ እንብዛም ግልፅ አልሆነም። በተለያዩ የጀርመን ከተሞች ሰሞኑን በፔጊዳ ስር አደባባይ የሚወጡት ሰዎች በግልፅ የሚናገሩት፤ ወደ ጀርመን የውጭ ሀገር ሰዎች እንዲመጡ እንደማይፈልጉ፤ የእስልምና እምነት ጨርሶ ቦታ እንደሌለው እና ፤ ነፃነት የሚሰማቸው፤ ጀርመን የጀርመናውያን ብቻ ሆና ስትቆይ እንደሆነ ይናገራሉ።

የፔጊዳ ሰልፈኛ አደባባይ የወጣበት ከተማ ፤ ድሬስድን ናት። እንደሚታወቀው ድሬስድን የውጭ ሀገር ዜጋው ቁጥር ከመቶ 4,7 ነው። የድሬስድን ከተማ የምትገኝበት የዛክስን ግዛት እንኳን ከአንድከመቶ ያነሰ የእስልምና ተከተማይ የሚኖርባት የጀርመን ግዛት ነች። ታድያ የህብረተሰቡ ተቃውሞ ከምን የመነጨ ነው?

Pegida-Kundgebung in Dresden
ምስል picture-alliance/dpa/Kay Nietfeld

በርካታ የቀኝ ፅንፈኞች ተቀላቅለውት ይሆናል የሚባለው የፔጊዳ ህብረት በአጭር ጊዜ ውስጥ በውጭ ዜጎች ላይ ጥላቻን የሚያንፀባርቁ ጀርመናውያንን ለማነሳሳት ችሏል። በጀርመን ምናልባት በይፋ ከሚገመተው በላይ ናዚዎች ይኖራሉ ማለት ነው? የፖለቲከኞቹስ አቋም ምን ይመስላል። የፔጊዳን እንቅስቃሴ ከበርሊን የተከታተለው ይልማ ኃይለ ሚካኤል ለጥያቄዎቹ ምላሽ ሰጥቶናል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ